ለትግራይ ክልል በአለም አቀፍ ድርጅቶች በኩል አስፈላጊ የህክምና መድሃኒቶችን የማድረሱ እንቅስቃሴ እንደቀጠለ ነው

  • Time to read less than 1 minute
 supplies

የኢትዮጵያ መንግስት ከሚሰራቸው ቀዳሚ ተግበራት መካከል የጤና አገልግትን ለሁሉም ዜጎች ማድረስ አንደኛው ሲሆን በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግስትም እያንዳንዱ ዜጋ የጤና አገልግሎት የማግኘት ጉዳይን በግልጽ ተጠቅሷል፡፡


ስለሆነም ዜጎች  የጤና አገልግሎት በፍትኃዊነት የማግኘት መብት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ የፖሊሲ አቅጣጫዎች በኢፊዲሪ የጤና ፖሊሲ ተካተዋል፡፡


ከዚህ አኳያ በአገራችን በተከሰቱ ግጭቶች ምክንያት ዜጎች የጤና አገልግሎቶችን የማግኘት ሰብዓዊና  ህገ መንግስታዊ መብቶች እንዳይስተጓጎሉ የኢትዮጵያ መንግስት በተለያዩ ጊዜያት ከአለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ለጤና አገልግሎት አስላፈጊ የሆኑ ድጋፎችን የማድረስ ተግበራትን  አከናውኗል፣ እያከናወነም ይገኛል፡፡


የኢትዮጵያ መንግስት ከጥር እስከ ሐምሌ 2022 ባለው ጊዜ ውስጥ ጤና ሚኒስቴር ፤ ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ፣ ከአለም አቀፍ አጋር ድጅቶች ጋር በቅርበት በመስራት ለትግራይ ክልል አስፈላጊ የሆኑ መድሃኒቶችን እና የአልሚ ምግብ አቅርቦቶችን የማመቻቸትና የማድረስ ስራዎች በማከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡


ከጥር እስከ ሀምሌ ባለው ጊዜ ውስጥ መንግስት በተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲዎች እና በአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ቻርተር እና መደበኛ በረራዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የመድሃኒት እና የስነ-ምግብ አቅርቦቶችን አመቻችቶ ለትግራይ ክልል አስረክቧል።

 

  • በጤና ሚኒስቴር በኩል ከጥር ወር ጀምሮ በድምሩ ብር 71,179,802.45 ዋጋ ያላቸው መድሃኒቶች እና የህክምና ቁሳቁሶች ወደ ትግራይ ክልል ተልከዋል፡፡ የተላኩ ዋና ዋና ነገሮችም ፡-
    • የፀረ-ቲቢ፣ የፀረ-ወባ፣ የልብ ህክምና መድሐኒቶች፣ የማደንዘዣ መድሃኒቶች፣ የሄሞዳያሊስስ መገልገያ ቁሳቆሶች ፣ ክትባቶች ፣የኮቪድ-19 አቅርቦቶች እና ሌሎች አስፈላጊ መድሃኒቶች።
    • ለ1,128,750 ግለሰቦች ለ3 ወራት አገልግሎት መስጠት የሚችሉ 135.45 ሜትሪክ ቶን የጤና እና አልሚ ምግብ አቅርቦቶች ለአስፈላጊ  የጤና አገልግሎቶች ወደ ትግራይ ክልል ተልኳል፡፡
  • ከዚህ ውስጥ በሁለት ወራት ማለትም  በሰኔ እና ሀምሌ  ወራት /2022
    • ግምታቸው ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ  ዋጋ ያላቸው መድሀኒት እና የህክምና ቁሳቁሶችን ወደ ትግራይ ክልል ተልከዋል።
  • በአጋር ድርጅቶች በኩል የተደረጉ ድጋፎች
    • ባለፉት ስድስት ወራት 76 ሜትሪክ ቶን የህክምና አቅርቦቶችም  በአጋር ድርጅቶች በኩል ወደ ትግራይ ክልል ተልከዋል፡፡  በዚህም እንደ UNICEF, Samaritans Purse, Goal Ethiopia, Save the children, Catholic relief service, CRS, Medical team international, World Vision, UNFPA, UNHCR, IOM, SCI, Plan international, MSF-H ተሳትፈውበታል፡፡
    • ሰሞኑንም የዓለም ጤና ድርጅት በጤና ሚኒስቴር በኩል የሚሰራጭ 1.04 ሜትሪክ ቶን የጸረ-ቲቢ መድኃኒቶች በአስቸኳይ ቻርተርድ UNHAS በረራ ወደ ትግራይ እንዲጓጓዝ የተመቻቼ ሲሆን 55 ሜትሪክ ቶን የህክምና ቁሳቁሶች እና አቅርቦቶች በዚህ ሳምንት ወደ ትግራይ ለመላክ  ቅድመ ዝግጅቶች ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል።
    • ባለፉት ስድስት ወራት ለ804,584 ግለሰቦችን ለ3 ወራት ሊያገለግል የሚችል  96.55 ሜትሪክ ቶን  አስፈላጊ መድሃኒት  በICRC በኩል ድጋፍ ተደርጓል፡፡ በሁለት ወራት ውስጥ ከICRC አክሲዮን እና ጤና ሚኒስቴር/ከኢትዮጵያ መድሓኒት አቅራቢ አገልግሎት የክምችት ማዕከላት ከ38.45 ሜትሪክ ቶን በላይ ግምት ያላቸው መድሃኒት እና የህክምና አቅርቦቶች  የማጓጓዝ ስራውን ማመቻቼት ተችሏል፡፡
    • ከICRC ድጋፍ በተጨማሪ ከተለያዩ ለጋሽ ድርጅቶች (GE, EPA etc) የተሰበሰቡ ድጋፎች በቅርቡ ወደ ትግራይ ክልል የሚላክ ይሆናል፡፡

በአጠቃላይ ላለፉት ስድት ወራት ከጤና ሚኒስቴርና እና አጋር ድርጅቶች 308 ሜትሪክ ቶን የሚሆን የጤና ቁሳቁሶች ተጓጉዘዋል። በቀጣይም አስፈላጊ መድሃኒት እና ግብዓት ተደራሽ ለማድረግ ስራዉ ተጠናክሮ ይቀጥላል።


ጤና ሚኒስቴር ፣ኢትዮጵያ