በዛሬው ዕለት የችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት (በገፈርሳ የአዕምሮ ህሙማን ማገገሚያ ማዕከል) የተከናወነ ሲሆን በ2014 ዓ.ም ክረምት ወራት የጤና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ከ50 ሺ በላይ ችግኞችን ለመትከል ወደ ተግባር መግባቱን የጤና ሚኒሰቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት (በገፈርሳ የአዕምሮ ህሙማን ማገገሚያ ማዕከል 20 ሺህ ለምግብነት የሚውሉ ችግኞች የመትከሉ መርሀ ግብር የተከናወነ ሲሆን በተጨማሪም በማእከሉ የተከናወኑ የልማት እና የማስፋፊያ ስራዎች የወተት ልማትን ጨምሮ የከተማ ግብርናን የመተግበር ስራ እንዲሁም የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ተጎብኝተዋል። ይህም ተግባር በማዕከሉ ያለውን የምግብ አቅርቦት በራስ አቅም ለመሸፈን ያስችላል ተብለዋል።
ክብርት ሚኒሰቴር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በንግግራቸው ለአራተኛ ግዜ የሚከናወነው ኢትዮጵያን አርንጓዴ የማልበስ ተግባር በተለይ ለጤናው ዘርፍ ያለው አበርክቶ ሰፊ በመሆኑ በትኩረት የምናከናውነው ተግባር ነው ብለው በኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት ቅጥር ግቢ ውስጥም ለምግብነት የሚውሉ አትክልትና ፍራፍሬ ችግኞች መተከላቸውን ገልጸው ይህም በሽታን ለመከላከል እንደሚረዳ እና የተመጣጠነ ምግብ ለህሙማን ተደራሽ ከማድረግ ከፍተኛ ድርሻ ስላለው በትኩረት የሚከናወን መሆኑን ጠቁመዋል።
በኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ታሪኩ ታደሰ እንደተናገሩት በማዕከሉ "አሻራችን ለትውልዳችን" በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ መረሃግብር መደረጉ የተተከሉ ችግኞችን በቅርበት ለመንከባከብና የአቅመ ደካሞችን ቤቶችን ማደስ እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ተማሪዎችን በትምህርት ቁሳቁስ የመደግፍ ሰራዎች እንድሚሰሩም ተጠቁመዋል።