የጤና ሚኒስቴር በአዲስ መልክ ያበለፀገውን ዌብ ሳይት ይፋ አደረገ

  • Time to read less than 1 minute
website

አዲሱ ዌብ ሳይት ሁለገብና መረጃዎችን በተደራጀና ሳቢ በሆነ መንገድ ለተጠቃሚዎችና ለባለድርሻ አካላት የሚያደርስ መሆኑን የገለፁት ዌብ ሳይቱ እውን መሆኑን ያስተዋወቁት በጤና ሚኒስቴር የሚኒስትሯ ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር ዳንዔል ገብረሚካኤል ናቸው።


የቀድሞው ዌብ ሳይት መረጃ እንደልብ የማይገኝበትና ሳቢ እንዳልነበረ ቅሬታ የሚቀርብበት ነበር ያሉት ዶ/ር ዳንዔል አዲሱ ዌብ ሳይት በተገቢ መረጃዎች የተደራጀና ለአጠቃቀም ሳቢ እና ቀላል ሆኖ የቀረበ ሲሆን ማንኛውም  ከሀገር ዉጪም ሆነ በሀገር ውስጥ ለሚገኙ ተገልጋዮች የኢ ላይብረሪ ፣ኦን ላይን የበጎ ፈቃድና ልገሳ አገልግሎት፣ የአስተያየት/ቅሬታ ማቅረቢያ፣ የቴሌቪዥን ቻናል፣ የዲጂታል ጤና ሲስተሞች፡ የጤና ማህበራት የጥናትና ምርምር ውጤቶችን እና ሌሎችንም ያካተተ መሆኑ ተገለጿል።


አዲሱ የሚኒሰቴሩ ዌብ ሳይት ይፋ የሆነውና ስራ እንደጀመረ የተገለፀው በጅግጅጋ ከተማ እየተከሄደ ባለው 23ኛው የጤናው ዘርፍ የምክክር  ጉባዔ ላይ ሲሆን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ለአዲሱ ዌብ ሳይት መበልጸግ እና ዕውን መሆን የተረባረቡትን ሁሉ አመስግነዋል ።