የመድኃኒትና ህክምና መሣሪያዎች መሪ ስራ አስፈፃሚ

ዓላማ

  • ጠንካራና ምላሽ ሰጪ የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደር ማቋቋም
  • አግባባዊ የሕክምና መሣሪያ አስተዳደር ስርዓት መዘርጋት
  • ምላሽ ሰጪ የአደጋ ጊዜ አቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደርን መዘርጋት
  • በጤና ተቋማት የፋርማሲ አገልግሎት ማጠናከር
  • የባህላዊ ህክምናን ከዘመናዊ ህክምና አገልግሎት ጋር ማቀናጀት

ራዕይ

  • ጥራታቸው የተረጋገጡ እና ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው መድኃኒትና የህክምና መሳሪያዎች ዘላቂ አቅርቦትን ማረጋገጥ፣ አግባባዊ የመድኃኒት አጠቃቀም ማረጋገጥ እንዲሁም ባህላዊ ህክምናን ከዘመናዊ ህክምና ጋር ማቀናጀት

ተልዕኮ

  • ጠንካራ፣ ምላሽ ሰጪ እና ውጤታማ የመድኃኒትና የሕክምና መሣሪያ አቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደርና የፋርማሲ አገልግሎት ስርዓት መተግበር

    የመድኃኒትና ህክምና መሣሪያዎች  መሪ ስራ አስፈፃሚ ተግባር እና ኃላፊነት

  1. በህክምና ግብዓት እና መሣሪያዎች ዘርፍ ስትራቴጂ፣ ፖሊሲ፣ መመሪያ፣ ፕሮቶኮል፣ ፍኖተካርታ እና መደበኛ የአሰራር ሂደት ማዘጋጀትና በአግባቡ መፈጸሙን መከታተል
  2. ሀገር አቀፍ የመሰረታዊ መድኃነቶችና የህክምና መሣሪያዎች መዘርዝር፤ መደበኛ የህክምና አሰጣጥ መምሪያ (STG)፤ የመድኃኒት ፖሊሲ ማዘጋጀትና በወቅቱ ክለሳ ማድረግ እንዲሁም ትግበራውን መከታተል
  3. የጤና ፕሮግራም የአቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደር ስርዓትን መምራት
  4. በጤና ተቋማት የክሊኒካልና ፕሮግራም ተኮር የፋርማሲ አገልግሎት እንዲኖር፤ የማህበረሰብ መድኃኒት ቤት እንዲስፋፋ፤ የመድኃኒት ቅመማ አገልግሎት እንዲጠናከር እንዲሁም ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው የህክምና ግብዓት ዝውውርና አገልግሎት እንዲኖር ድጋፍና ክትትል ማድረግ፤ ማስተዋወቅና ማስተግበር
  5. በሁሉም ደረጃ ትክክለኛ የመድኃኒት አወሳሰድ እንዲኖር ማበረታታት እና የፀረ-ተህዋስያን መድኃኒቶች በጀርሞች መለመድ፤ መከላከልና መቆጣጠር ስራዎችን መምራት እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ማስታባበር
  6. ጤና ተቋማት አመታዊ የመድኃኒት ምጠና እንዲሰሩ መደገፍ እና ማስተባበር
  7. በጤና ተቋማት መሰረታዊ መድኃኒቶች፣ የህክምና ግብዓቶችና ሪኤጀንቶች እንዲኖሩ ድጋፍና ክትትል ማድረግ
  8. በሀገር ውስጥ የህክምና ግብዓትና መሣሪያዎች ምርትን ማበረታታት
  9. በመድኃኒትና በህክምና መሣሪያዎች እንዲሁም በባህላዊ ህክምና ዙሪያ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ማጠናከር
  10. በህክምና ግብዓቶች አቅርቦት ሰንሰለት፤ በባህላዊ ህክምና፤ በህክምና መሣሪያዎች አጠቃቀም፣ አያያዝና ጥገና ለክልል ጤና ቢሮዎችንና ጤና ተቋማትን አቅም ማጎልበት
  11. መድኃኒትና ህክምና መሣሪያዎች አቅርቦትን ለማሻሻል እና ውጤታማ አስተዳደር እንዲኖር ማድረግ እንዲሁም ለድንገተኛ ሁኔታዎች በህክምና ግብአቶች ላይ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ከባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት መስራት
  12. በህክምና ግብዓቶች አቅርቦት ሰንሰለት፣ በፋርማሲ አገልግሎት፣ በባህላዊ ህክምና እና በህክምና መሣሪያዎች አስተዳደር ዙሪያ አስፈላጊ ጥናቶች ከዩኒቨርሲቲዎች እና አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር እንዲሰሩ ማስተባበር
  13. የኦክሲጅን ማምረቻ ለፕላንቶችን ማስፋፋት እንዲሁም የተከላና ጥገናን ስራዎችን መከታተል
  14. ሀገር አቀፍ የህክምና ግብዓትና ህክምና መሳሪያዎች መረጃ ስርዓትን ማጠናከር
  15. የሕክምና መሳሪዎችን እቅድ፣ የፍላጎት ጥናት፣ የግዥ፣ የተከላ፣ የጥገና፣ የአወጋገድና የኮንትራት ትግበራን መከታተልና መደገፍ
  16. የህክምና መሣሪያዎች ጥገናና እድሳት የልህቀት ማዕከል እንዲቋቋም ማስተባበር
  17. የባህላዊ ህክምና ከዘመናዊ ህክምና ጋር በጥምረት እንዲሰራ ማበረታታት
  18. ሀገር አቀፍ የባህላዊ ህከምና፤ የፀረ ተህዋፅያን ብግርነት መከላከል እና የህክምና ግብዓት ስርዓት መማክርት ጉባኤ መምራት እና ማስተባበር