ራዕይ
- የስርዓተ-ምግብ ዋስትናቸው የተረጋገጠ ጤናማ ህይዎት ያላቸው አምራችና እረጅም እድሜ ያላቸው ኢትዮጵያውያንን ማየት
ተልእኮ
- ቀጥተኛና ሥርዓተ-ምግብ ተኮር ሴክተሮች ቅንጅታዊ አሰራርን በማረጋገጥ የምግብና ሥርዓተ-ምግብ ዋስትናን ማስፈን ነው።
ግብ
- በሁሉም ዕድሜ ክልልና ሁኔታ ለሚገኙ ዜጎች ጤናማ ህይወት፣ አምራችነትና ረዥም እድሜ እንዲኖራቸው የሚያስችል የሥርዓተ- ምግብ ደረጃ ላይ ማድረስ ነው።
ስትራቴጅያዊ አላማዎች
ምቹ የሆነ የፓሊሲ ከባቢ በመፍጠር እና የምግብ እና የስርዓተ-ምግብ ፓሊሲውን ስትራቴጅያዊያዊ አቅጣጫዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ የምግብ እና የስርዓተ-ምግብ ስትራቴጅ የሚከተሉት ስትራቴጅያዊያዊ አላማዎች አሉት
አላማ 1፡- በቂ የሁሉም የምግብ ክፍሎች የተወጣጣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና በንጥረ ምግቦች የበለፀገ ምግብን አቀርቦትን እና ተደራሽነትን ለዜጎች በዘላቂነት ማሻሻል
አላማ 2፡- የተቀናጀ እና ጠንካራ የምግብ ደህንነት እና ጥራት ሰንሰለት መዘርጋትና መፈፀም
አላማ 3፡-በድህረ-ምርት የእሴት ሰንሰለት ውስጥ ያለውን የምግብ አያያዝ ማሻሻል
አላማ 4፡- ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆኑ የስርዓተ-ምግብ ትግበራዎች አማካኝነት በአንድ ሰው የህይዎት ኡደት ውስጥ ባሉ በሁሉም ደረጃዎች ያለውን የስርዓተ-ምግብ ሁኔታን ማሻሻል፡፡
አላማ 5፡- ተላላፊ፣ ተላላፊ ያልሆኑ እና ከኑሮ ዘይቤ ጋር ግንኙነት ያላቸው በሽታዎች የተያዙ ሰዎችን የስርዓተ ምግብ ሁኔታ ማሻሻል
አላማ 6፡- አገሪቱ የምግብ እና ስርዓተ-ምግብ ችግርን ሊሚያባብሱ ለሚችሉ የተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ ድንገተኛ አደጋዎች ያላትን ዝግጁነት እና አያያዝ እንዲሁም ለአደጋው ተፈናቃዮች እና ስደተኞችን ጨምሮ ተገቢ እና ወቅቱን የጠበቀ ምላሽ የመስጠት አቅም ማጠናከር
አላማ 7፡- የግለሰብ፣ የቤተሰብን እና የተቋማትን የውሃ አቅርቦት፣ የግል እና የአካባቢ ንፅህናን (WASH) ማሻሻል
አላማ 8፡- በቂ ደህንነቱ የተጠበቀ ሁሉንም የምግብ ክፍሎች የያዘ እና በንጥረ ምግቦች የበለፀገ ምግብ አወሳሰድን የተመለከተና መረጃን መሰረት ያደረገ ውሳኔ መወሰን እንዲችሉ በምግብ እሴት ሰንሰለት ውስጥ ያሉ የግለሰቦች፣ ቤተሰቦችና የማህበረሰቡን የስርዓተ ምግብ ግንዛቤ ማሳደግ
አላማ 9፡- በምግብ እና ስርዓተ-ምግብ ፓሊሲ ፈፃሚ ሴክተሮች መሃል ትብብር እና ቅንጅትን የሚያጠናክር ውጤታማ የስርዓተ-ምግብ አስተዳደርን ማቋቋም
አላማ 10፡- የምግብ እና የስርዓተ-ምግብ ፓሊሲውን ወደ ተግባር ለመቀየር ያስችል ዘንድ ከመንግስት መጀት፣ ከግል ሴክተሩ፣ ከማህበረሰቡ ከልማት አጋሮች እና ሌሎእ አዳዲስ ምንጮች በቂ እና ዘላቂ የሆነ የገንዘብ አቅም የሚያስገኝ ስርዓት መዘርጋት እና ማሻሻል
አላማ 11፡- የምግብ እና የስርዓተ-ምግብ ፈፃሚ ሴክተሮችን ተቋማዊ አቅም በሰው ሀይል በጥናትና ምርምር እና ቴክኖሎጅዎች ዘርፍ ማጎልበት
አላማ 12፡- በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ሰጭነት ትምህርት አወሳሰድን እና ተጠያቂነትን ማጠናከር
አላማ 13፦ ለምግብ እና ስርዓተ ምግብ ውጤታማ የሆነ ተግባቦት መዘርጋት
የሥርዓተ-ምግብ ማስተባባሪያ ጽ/ቤት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዋና ዋና ተግባራት እና ውጤቶች
በጤና ሚኒስቴር በሶስት ዴስኮች የተዋቀረው አዲሱ መዋቅር በሀገሪቱ የምግብና ስርዓተ ምግብ ስራዎች አስፈፃሚ አካል ሲሆን ለሚኒስትሯ ቀጥተኛ ተጠሪነት አለው በዋናነትም የሚከተሉት ዋና ዋና ተግባራትን ያከናውናል፡፡
1፦መከላከል-ተኮር ሥርዓተ-ምግብ አገልግሎት አሰጣጥን መምራት፣
- ለቅድመ-እርግዝና፣ ለወጣቶች እና አፍላ ወጣቶች፣ ለነፍሰጡርና የሚያጠቡ እናቶች፣ በትምህርት እድሜ ክልል ላሉ ታዳጊ ልጆች (6-10 ዓመት) የሚሰጡ የሥርዓተ-ምግብ አገልግሎቶች ፓኬጅ ዝግጅትና አገልግሎት አሰጣጥን ይመራል፡፡
- በሁሉም የጤና ተቋማት እና በሌሎች የሥራ ቦታዎቸ የጡት ማጥባት ክፍሎች እንዲደራጁ ያስተባብራል፤ ይመራል፡፡
- ለሕጻናት መልካም አካላዊና አእምሯዊ ዕድገት ወሳኝ የሆነውን የእናት የጡት ማጥባት ባህልን የሚጎዱ የወተት ንግድ ማስታወቂያዎች እንዳይተላለፉ ከሚመለከታቸው ጋር በትብብር ይሠራል፣ ኅብረተሰቡም ግንዛቤ እንዲፈጠር ያስተባብራል፣ ይከታተላል፣ ይመራል፡፡
- የእድገት ክትትልና ማበልፅግ፣ የጥቃቅን ንጥረ-ምግቦች እና የአንጀነት ጥገኛ ትላትል መድሃኒቶች እደላ አገልግሎቶች ተደራሽ እንዲሆኑ ያስተባብራል፣ ይከታተላል፣ ይገመግማል፡፡
- የምግብ ደህንነትና ጥራት ላይ የህበረተሰቡን እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ግንዛቤ ለማሳደግ የሚያግዙ ዝርዝር የጥንቃቄ እና የመከላከል መልዕክቶችን ዝግጅትና ስርጭት በበላይነት ያስተባብራል፡፡
- የጥቃቅን ንጥረ-ምግቦች እጥረትን ለመከላከል ምግብን በአልሚ ንጥረ-ነገሮች ለማበልፀግ የተቀየሱ ስልቶችንና ደረጃዎችን ትግበራ ይመራል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፡፡
- በጥናት ላይ የተመሠረተ መከላከል-ተኮር የሥርዓተ-ምግብ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ እና የአገልግሎት ጥራትን ለማረጋገጥ ፓኬጆችና ስታንዳርድ ዝግጅት ያስተባብራል፤ አግባብነት ያለው ስርዓት እስከ ማህበረሰብ ደረጃ እንዲዘረጋና ተግባራዊ እንዲሆን አመራር ይሰጣል፡፡
2፦ አጣዳፊ መካከለኛ እና ከፍተኛ የምግብ አለመመጣጠን የምገባ-ህክምና አገልግሎት መምራት፣
- የአጣዳፊ የምግብ አለመመጣጠን ተጋላጭነትን ለመቀነስ እና ወቅታዊ ምላሽ ለመስጠት የሥርዓተ ምግብ የቅድመ-ማስጠንቀቂያና ልየታ ሥርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፡፡
- የአጣዳፊ መካከለኛ እና ከፍተኛ የምግብ አለመመጣጠን የምገባ-ህክምና አገልግሎት የሚሰጡ ጤና ተቋማት ዝግጁ እንዲሆኑ ያስተባብራል፣ ይከታተላል፣ ይገመግማል፡፡
- ለአጣዳፊ የምግብ አለመመጣጠን ችግር ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን (ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች፣ ከ5 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት፣ ታዳጊዎች፣ አረጋዊያን፣ የተፈናቀሉ ማህበረሰቦች፤ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ያሉባቸው ሰዎች) የሥርዓተ-ምግብ ሁኔታ ልየታ (nutritional screening) እንዲካሄድና የአገልግሎት ቅብብሎሽ የተሳለጠ እንዲሆን ያስተባብራል፣ ይከታተላል፣ ይገመግማል፡፡
- የከፍተኛ አጣዳፊ የምግብ አለመመጣጠን ተጠቂ ሰዎች በጤና ተቋማት ተኝተው እና በተመላላሽ ምገባ-ሕክምና (therapeutic feeding programme) ወይም የመካከለኛ አጣዳፊ የምግብ አለመመጣጠን ተጠቂ ሰዎች በማህበረሰብ ደረጃ የተጨማሪ ምገባ-ህክምና (supplementary feeding programme) አገልግሎት በተቀናጀ ሥርዓት ተደራሽ እንዲሆን ያስተባብራል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፡፡
- የሥርዓተ-ምግብ ዝግጁነት ለማጠናከር የአጣዳፊ የምግብ አለመመጣጠን የምገባ-ሕክምና ድንገተኛ ምላሽ አስፈላጊ የሰብዓዊ ፍላጎት ሰነድ (humanitarian appeal document) ዝግጅትና ትግበራ ያስተባብራል፣ ይከታተላል፡፡
3፦የዘርፈ-ብዙ እና ሰቆጣ ቃል-ኪዳን ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር፣
- ዓመታዊ በበጀት የተደገፈ የተዋሃደና የተቀናጀ የዘርፈ-ብዙ እና ሰቆጣ ቃል-ኪዳን ዕቅድ ዝግጅት ያስተባብራል፣ አፈጻጸሙን በስኮር ካርድ ይከታተላል፣ ሪፖርት ለአስተባባሪ ም/ቤት ያቀርባል፡፡
- የተቀናጀ የሥርዓተ-ምግብ መረጃ ሥርዓት እንዲዘረጋና እንዲተገበር ያስተባብራል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፡፡
- የተሻሉ ተሞክሮዎችንና የዓለም-አቀፍ ምክረ-ሀሳቦችን እንዲቀመር እና እንዲሰፋ ያስተባብራል፣ ይደግፋል፣ ይከታተላል፣ ይገመግማል፡፡
- የዘርፈ-ብዙ እና ሰቆጣ ቃል-ኪዳን በሙከራ ትግበራ ምዕራፍ የተገኙ የማህበረሰብ ንቅናቄ፣ መማማሪያ እና ሰርቶ ማሳያ (Community lab)፣ የአመራር ተሳትፎና ባለቤትነት ልምዶች መነሻ በማድረግ በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች በማስፋት ትግበራ ምዕራፍ እንዲተገበሩ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፣ ያስተባብራል፡፡
- መንግስታዊና መንግታዊ ያልሆኑ አካላት እንዲሁም ከግሉ ዘርፍ ጋር የሚደረጉ የስራ ግንኙነቶችን ተቋሟዊ ቅንጅትን ያስተባብራል፡፡
- ከሴክተር መ/ቤቶች ጋር በመተባበር የአጣዳፊ የምግብ አለመመጣጠን የመከላከልና የምገባ-ህክምና አገልግሎቶች ለተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ የሚከናወኑ ተግባራት ይመራል፣ ይከታተላል፣ ይገመግማል፡፡
- የብሔራዊ ምግብና ሥርዓተ-ምግብ አስተባባሪ ምክር ቤት ሰክሬታሪያት ሆኖ ይሰራል፡፡
- ለብሔራዊ የምግብና ሥርዓተ-ምግብ አስተባባሪ ምክር ቤት እና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በሥርዓተ-ምግብ ላይ የሚያማክር የቴክኒክ ኮሚቴ በሁሉም ደረጃዎች እንዲደራጁ ያደርጋል፤ ይደግፋል፣ ይመራል፡፡
- የምግብና ሥርዓተ-ምግብ ተግባሪ ሴክተሮች ድርሻ እና ሃላፊነት ዝርዝር የሚገልጽ የብዘሃ ሴክተር ማስተባባሪያ ሰነድ ዝግጅት ያስተባብራል፣ ለተግባሪ ሴክተሮችና ተቋማት ድጋፍ ይሰጣል፣ ይከታተላል፡፡
4 ለሥርዓተ-ምግብ አገልግሎቶች የሚውል ሃብት ማሰባሰብ፣ አቅርቦቶችና ግብዓቶችን ማሟላት፣
- ለሥርዓተ-ምግብ ፕሮግራም ትግበራ የገንዘብ፣ የቴክኒክ፣ የአቅርቦት እና የግብዓት ክፍተት ልየታን ያስተባብራል፣ በክፍተቱ ላይ በመመስረት የሃብትና ግብዓት ዕቅድ እንዲዘጋጅ ይመራል፡፡
- በሃብት ክፍተት ዕቅድ መሰረት ፕሮፖዛል እንዲዘጋጅ ያስተባብራል፣ ለለጋሽ አካላት ያቀርባል፣ ይደራደራል፣ ክትትል ያደርጋል፣ ሃብት የተገኝባቸው ሥራዎችን ሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣ የአፈፃፀም ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፣ ይገመግማል፡፡
- የድንገተኛና አጣዳፊ የምገባ-ህክምና ግብዓት የሚያመርቱ፣ የሚያቀርቡ እና የሚያከፋፍሉ የሀገር ውስጥና የውጪ አካላትን እንዲለዩ ያስተባብራል፣ ያለባቸውን ችግሮች መሰረት በማድረግ ስትራቴጂክ ምክረ-ሃሳብ ያቀርባል፡፡
- የምገባ-ህክምና ግብዓቶች አስተማማኝ አቅርቦትን ለማረጋገጥ እና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገኙ በሀገር ውስጥ የሚመረቱበትን ሁኔታዎች ያመቻቻል፣ ለአምራቾች ማበረታቻ እንዲደረግ ያስተባብራል፡፡
- ለጥቃቅን ንጥረ-ምግቦች ዕጥረት መከላከልና ሕክምና እንዲሁም ለአጣዳፊ የምግብ አለመመጣጠን ችግር ምገባ-ህክምና የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ክፍተት ትንበያና ዕቅድ ዝግጅት ይመራል፣
5። የፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ ፕሮግራሞች፣ መመሪያዎች፣ ማኑዋሎች ዝግጅት ማስተባበር፣
- የስትራቴጂክ ጉዳዮችን ልየታ፣ የፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ ፕሮግራሞች እና ስታንዳርዶች ዝግጅት ይመራል፣ በሚመለከተው አካል ያፀድቃል፣ በሥራ ላይ እንዲውሉ ያስተባብራል፣ አፈጻጸማቸውን ይደግፋል፣ ይከታተላል፣ ይገመግማል፡፡
- የሴክተሮች ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ዝግጅት ከምግብና ሥርዓተ-ምግብ ፖሊሲና ስትራቴጂ ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን ይከታተላል፣ ጥንካሬና ውስንነቶችን በመለየት ግብረ-መልስ ይሰጣል፡፡
- ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ከሃገራችን ተጨባጭ ሁኔታዎቸ ጋር በማዛመድ እንዲተዋወቁ እና ሥራ ላይ እንዲውል ያስተባብራል፣ ይከታተላል፤ ይገመግማል፡፡
- የዓለም-አቀፍ ስታንዳርድ መሠረት በማድረግ የአጣዳፊ የምግብ አለመመጣጠን ምገባ-ሕክምና የአገልግሎት ፓኬጅ እና መመሪያ ዝግጅትን ያስተባብራል፣ ሥራ ላይ እንዲውል ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፡፡
- የማህብረሰብ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልት እና መመሪያዎች ዝግጅትን ያስተባብራል፣ በሴክተሮችም እቅድ ተካቶ እንዲተገበር ይደግፋል፣ይከታተላል፡፡
- የጥናትና ምርምር ውጤቶችን መሰረት በማድረግ የምግብና ሥርዓተ-ምግብ የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ስትራቴጂክ ዝግጅት ያስተባብራል፡፡
- በምግብና ሥርዓተ-ምግብ አገልግሎት ተጠቃሚዎች እና ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች በጥናት የተደገፈ የምገባ-ሕክምና ፓኬጅ እና ስታንዳርድ ዝግጅት ያስተባብራል፡፡
6 ወረርሽኝና ድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎችን የመከላከል፣ የመቆጣጠር እና ምላሽ የመስጠት ስራዎችን ማከናወን፤
- የህብረተሰብ ወረርሽኝና ድንገተኛ አደጋ ሲከሰት በቦታው በመገኘት የህክምና ዕርዳታ እና የጤና ምክር ይሰጣል፡፡
- ህብረተሰብ-አቀፍ ወረርሽና የድንገተኛ አደጋዎች ላይ ቅኝትና ምላሽ ላይ በመሳተፍ ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
- የማህበረሰብ ንቅናቄ ውይይት ያካሂዳል፣ ማህበረሰቡን ያስተባብራል፣ የማህበረሰብ ባሌቤትንነትን ያጎለብታል፡፡
- የማህበረሰቡን ከድንገተኛ አደጋ ማንቂያ መልዕክቶችን በመቅረፅ ግንዛቤ ያሰርጻል፡፡
- ዘርፈ ብዙ ምላሽ በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ የሚመለከታቸውን ተቋማት በሚላሽ አሰጣጡ ላይ እንዲሳተፍ ያደርጋል፡፡
- የህክምና ግብዓትና ቁሳቁሶችን ያሟላል፡፡
- ድህረ ወረርሽኝና የድንገተኛ አደጋ ተጎጅዎችን መልሶ ማቋቋም ተግባራትን ያከናውናል፡