ዓላማ
- ጠንካራና ምላሽ ሰጪ የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደር ማቋቋም
- አግባባዊ የሕክምና መሣሪያ አስተዳደር ስርዓት መዘርጋት
- ምላሽ ሰጪ የአደጋ ጊዜ አቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደርን መዘርጋት
- በጤና ተቋማት የፋርማሲ አገልግሎት ማጠናከር
- የባህላዊ ህክምናን ከዘመናዊ ህክምና አገልግሎት ጋር ማቀናጀት
ራዕይ
- ጥራታቸው የተረጋገጡ እና ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው መድኃኒትና የህክምና መሳሪያዎች ዘላቂ አቅርቦትን ማረጋገጥ፣ አግባባዊ የመድኃኒት አጠቃቀም ማረጋገጥ እንዲሁም ባህላዊ ህክምናን ከዘመናዊ ህክምና ጋር ማቀናጀት
ተልዕኮ
- ጠንካራ፣ ምላሽ ሰጪ እና ውጤታማ የመድኃኒትና የሕክምና መሣሪያ አቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደርና የፋርማሲ አገልግሎት ስርዓት መተግበር
የመድኃኒትና ህክምና መሣሪያዎች መሪ ስራ አስፈፃሚ ተግባር እና ኃላፊነት
- በህክምና ግብዓት እና መሣሪያዎች ዘርፍ ስትራቴጂ፣ ፖሊሲ፣ መመሪያ፣ ፕሮቶኮል፣ ፍኖተካርታ እና መደበኛ የአሰራር ሂደት ማዘጋጀትና በአግባቡ መፈጸሙን መከታተል
- ሀገር አቀፍ የመሰረታዊ መድኃነቶችና የህክምና መሣሪያዎች መዘርዝር፤ መደበኛ የህክምና አሰጣጥ መምሪያ (STG)፤ የመድኃኒት ፖሊሲ ማዘጋጀትና በወቅቱ ክለሳ ማድረግ እንዲሁም ትግበራውን መከታተል
- የጤና ፕሮግራም የአቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደር ስርዓትን መምራት
- በጤና ተቋማት የክሊኒካልና ፕሮግራም ተኮር የፋርማሲ አገልግሎት እንዲኖር፤ የማህበረሰብ መድኃኒት ቤት እንዲስፋፋ፤ የመድኃኒት ቅመማ አገልግሎት እንዲጠናከር እንዲሁም ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው የህክምና ግብዓት ዝውውርና አገልግሎት እንዲኖር ድጋፍና ክትትል ማድረግ፤ ማስተዋወቅና ማስተግበር
- በሁሉም ደረጃ ትክክለኛ የመድኃኒት አወሳሰድ እንዲኖር ማበረታታት እና የፀረ-ተህዋስያን መድኃኒቶች በጀርሞች መለመድ፤ መከላከልና መቆጣጠር ስራዎችን መምራት እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ማስታባበር
- ጤና ተቋማት አመታዊ የመድኃኒት ምጠና እንዲሰሩ መደገፍ እና ማስተባበር
- በጤና ተቋማት መሰረታዊ መድኃኒቶች፣ የህክምና ግብዓቶችና ሪኤጀንቶች እንዲኖሩ ድጋፍና ክትትል ማድረግ
- በሀገር ውስጥ የህክምና ግብዓትና መሣሪያዎች ምርትን ማበረታታት
- በመድኃኒትና በህክምና መሣሪያዎች እንዲሁም በባህላዊ ህክምና ዙሪያ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ማጠናከር
- በህክምና ግብዓቶች አቅርቦት ሰንሰለት፤ በባህላዊ ህክምና፤ በህክምና መሣሪያዎች አጠቃቀም፣ አያያዝና ጥገና ለክልል ጤና ቢሮዎችንና ጤና ተቋማትን አቅም ማጎልበት
- የመድኃኒትና ህክምና መሣሪያዎች አቅርቦትን ለማሻሻል እና ውጤታማ አስተዳደር እንዲኖር ማድረግ እንዲሁም ለድንገተኛ ሁኔታዎች በህክምና ግብአቶች ላይ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ከባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት መስራት
- በህክምና ግብዓቶች አቅርቦት ሰንሰለት፣ በፋርማሲ አገልግሎት፣ በባህላዊ ህክምና እና በህክምና መሣሪያዎች አስተዳደር ዙሪያ አስፈላጊ ጥናቶች ከዩኒቨርሲቲዎች እና አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር እንዲሰሩ ማስተባበር
- የኦክሲጅን ማምረቻ ለፕላንቶችን ማስፋፋት እንዲሁም የተከላና ጥገናን ስራዎችን መከታተል
- ሀገር አቀፍ የህክምና ግብዓትና ህክምና መሳሪያዎች መረጃ ስርዓትን ማጠናከር
- የሕክምና መሳሪዎችን እቅድ፣ የፍላጎት ጥናት፣ የግዥ፣ የተከላ፣ የጥገና፣ የአወጋገድና የኮንትራት ትግበራን መከታተልና መደገፍ
- የህክምና መሣሪያዎች ጥገናና እድሳት የልህቀት ማዕከል እንዲቋቋም ማስተባበር
- የባህላዊ ህክምና ከዘመናዊ ህክምና ጋር በጥምረት እንዲሰራ ማበረታታት
- ሀገር አቀፍ የባህላዊ ህከምና፤ የፀረ ተህዋፅያን ብግርነት መከላከል እና የህክምና ግብዓት ስርዓት መማክርት ጉባኤ መምራት እና ማስተባበር