የኮቪድ 19ን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲሁም የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም የሚያግዝ ሰው ሰራሽ መተንፈሻ መሳሪያ ድጋፍ ርክክብ ተደረገ
ግምታቸው 30 ሚሊዮን ብር የሚሆን 100 ሰው ሰራሽ መተንፈሻ መሳሪያዎች የኮቪድ 19ን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲሁም የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም የሚያግዝ ሰው ሰራሽ መተንፈሻ መሳሪያ ድጋፍ ለጤና ሚኒስቴር ተደርጓል፡፡
ድጋፉን ለጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ያስረከቡት የሞደርን ኢ.ቲ.ኤች አውት ሶርስ ፒ.ኤል.ሲ ተወካይ የሆኑት አቶ ታዲዮስ ተፈራ፤ ድጋፉ የተደረገው በኮቪድ የተጠቁ ዜጎችን ለመርዳት ታስቦ መሆኑን ገልጸው ድጋፋቸው የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ፣ ድጋፉን ያደረጉትን ድርጅቶች አመስግነው፤ መሳሪያዎቹ በጽኑ ህሙማን ማገገሚያ የሚገኙ ታካሚዎችን ለመርዳት ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርጉ ገልጸው ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።