"በግሎባል ፈንድ የሚተገበሩ ፕሮግራሞች ውጤት ተኮር በመሆናቸው ሁሉም አካል በትኩረት ሊሰራባቸው ይገባል።" የጤና ሚኒስትር ዴኤታ - ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ
ግሎባል ፉንድ ግራንት ፕሮግራም ትግበራ ሂደቶችን የመገምገም እና እስካሁን በተያዙ እቅዶች አፈጻጸም ላይ ያተኮረ ግምገማ ዛሬ በጤና ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡
የግምገማ መድረኩ በጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ የተመራ ሲሆን ትኩረቱንም እስካሁን ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከግሎባል ፈንድ በተገኝው የፋይናንስ ድጋፍ በጤናው ዘረፍ የተከናወኑ ዝርዝር ስራዎች ቀድሞ ከታቀደው እቅድ አኳያ አሁናዊ ደረጃው ምን እንደሚመስል እና የእቅድ አተገባበሩ ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የተገመገመበት ነው።
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ በግምገማ መድረኩ እንደተናገሩት በግሎባል ፈንድ የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች ውጤት ተኮር በመሆናቸው ሁሉም አካል በትኩረት ሊሰራባቸው እንደሚገባ አንስተዋል፡፡