ዩኤስኤአይዲ( USAID) 156 የጅን ኤክስፕርት ማሽኖች ድጋፍ ለጤና ሚኒስቴር አድርጓል
ድጋፉ ሶስት ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጪ የተደረገበት ሲሆን የቲቢ ፈጣን ሞለኪውላር ምርመራ በማድረግ የቲቢ በሽታን በፍጥነት ለማግኘት የሚያስችል ቴን ከለርድ የጂን ኤክስፐርት ማሽኖች ድጋፍ መሆኑ ታውቋል፡፡ በድጋፍ የተገኙት የጂን ኤክስፐርት ማሽኖቹ በተለይ ለተጎጂ ክልሎች እና የቲቢ ስርጭት ላለባቸው አካባቢዎች ላይ ላሉ ጤና ተቋማት እንደሚተላለፉ ተገልጿል።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ በድጋፉ የርክክብ ስነስርዓት ላይ እንደተናገሩት የጤና ሚኒስቴር የሳንባ ነቀርሳን ለማጥፋት አዲስ የ7 ዓመታት ስትራቴጂክ እቅድ ማዘጋጀቱንና ዩኤስኤአይዲ ኢትዮጵያ በአዲሱ ስትራቴጂክ ዕቅድ ውስጥ ቁልፍ ሚና እንደነበረው ጠቅሰው ለእቅዱ ስኬት መረጃን መሰረት ባደረገ፤ ውጤታማ በሆነ መንገድ መተግበርን ይጠይቃል ብሏል።