32 ሀገራት እየተሳተፉ ያሉበት የአፍሪካ መደበኛ ስፔሻላይዝድ የጤና፣ ስነ-ምግብ፣ ህዝብ እና መድሀኒት ቁጥጥር ውይይት በአፍሪካ ህብረት የስብሰባ አዳራሽ እየተካሄደ ነው
ውይይቱ “ጤናን ማዳበር በአፍሪካ፡ ሁለንተናዊ የጤና፣ የተመጣጠነ ምግብ፣ የህዝብ ቁጥር፣ የመድኃኒት ቁጥጥር፣ ወንጀል መከላከል እና ትምህርት ”በሚል መሪ ቃል የተካሄደ የሚገኝ ሲሆን ከአፍሪካ የልማት አጀንዳ ጋር በማጣጣም ከጤና፣ ከሥነ-ምግብ፣ ከሕዝብ እና ከመድኃኒት ቁጥጥር ጋር የተያያዙ በርካታ የሥራ ሰነዶችን ይጸድቃሉም ተብሎ ይጠበቃል።
በኮንፈረንሱ ከ32 አባላት የተውጣጡ ሚኒስትሮች እና ልዑካን ቡድኖች የተገኙ ሲሆን ከተለያዩ የአፍሪካ ህብረት አካላት እና አጋር ድርጅቶች ተወካዮች የተውጣጡ ኃላፊዎችና ባለሙያዎችም ተገኝተውበታል።
ከኢትዮጵያ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ እና የሚመለከታው ሌሎች የስራ ኃሌፊዎችና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል።