ራዕይ
"ሴቶች፣ ህጻናት፣ ወጣቶችና የተለያየ አይነት የአካል ጉዳት ያለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በጤናው ዘርፍ በእኩልነት ተሳትፈውና እስከ ከፍተኛ ደረጃ ባለ የጤና አገልግሎት ውስጥ ጥራቱን በጠበቀና ፍትኃዊ በሆነ መልኩ ተጠቃሚ ሲሆኑ ማየት።"
ተልዕኮ
ከሴቶች፣ ህጻናት፣ ወጣቶችና ከአካል ጉዳተኞች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ትኩረት እንዲሰጣቸው እና በጤናው ሴክተር በሚተገበሩ ፖሊሲዎችና ፕሮግራች ውስጥ እንዲካተቱ እንዲሁም ሴቶች የውሳኔ ሰጪነት ቦታዎችን እንዲይዙ የሚያስችል አቅም እንዳላቸው እንዲገነዘቡ ማስቻል ነው።
ቁልፍ ስልታዊ ዓላማዎች
የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ቁልፍ ስትራቴጂክ ዓላማ በሚከተሉት ዋና ዋና ትኩረቶች ላይ ያጠነጥናል፡-
- በየደረጃው የሚገኙ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ መዋቅሮችን ማጠናከር፣
- ሥርዓተ-ጾታን፣ ሴቶችን፣ ህፃናትን፣ ወጣቶችን እና አካል ጉዳተኝነትን በሁሉም ፕሮግራሞች፣ ስርዓቶች እና እንቅስቃሴዎች ውስጥ ማካተት፣
- ሴቶችና ወጣቶችን ማብቃት፣
- የህፃናት ጤና መብት ጥበቃ ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት፣
- ለሴት ሰራተኞች ምቹ የስራ ቦታን መፍጠር፣
- ለአካል ጉዳተኞች ምቹ እና ተደራሽ የሆነ የጤና አገልግሎት መፍጠር።
- ለአረጋውያን፣ ለጎዳና ተዳዳሪዎች፣ ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና ለማረሚያ ቤት ታራሚዎች አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ።
ለስትራቴጂካዊ ትግበራ ቁልፍ ግብአቶች
የሴቶች/ የልጃገረዶች፣ የወጣቶች፣ የህጻናት እና የአካል ጉዳተኞች የጤና ሁኔታን ለማሻሻል አንኳር ውጤቶች እየተመዘገቡ ይገኛሉ።
- በጤናው ዘርፍ ከሴቶች፣ ህጻናት፣ ወጣቶችና ከአካል ጉዳት ጋር በተያያዙ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ማካተት፣
- ለጤናው ዘርፍ ሰራተኞች አቅም ግንባታ፣
- ምርምርን ጨምሮ ስልታዊ መረጃዎችን ማዘጋጀትና እና መጠቀም፣
- በጤናው ዘርፍ የሴቶች፣ ህፃናት፣ የወጣቶች እና ከአካል ጉዳተኞች ጉዳይ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ማስተባበር፣
- በሁሉም የጤናው ዘርፍ መዋቅር የሴቶችን አቅም ማጎልበት፣
- አጋርነትን እና ትስስርን ማጠናከር፣
- የሀብት ማሰባሰብን በማመቻቸት ውጤታማ እና ቀልጣፋ የሀብት አጠቃቀም መፍጠር፣
- በስርዓተ-ፆታ ኦዲት አማካይነት የስርዓተ-ፆታ ጉዳይ መካተቱን ማረጋገጥ፣
- የህፃናት ማቆያን እና የጡት ማጥቢያ ኮርነሮችን በማዘጋጀት የህጻናት ጤና መብቶችን ማረጋገጥ፣
- የእስትራቴጂክ እቅድ በማዘጋጀት የፆታዊ ጥቃት መከላከልና የጤና ምላሽ ማረጋገጥ፣
- የተለያየ አይነት የአካል ጉዳት ላጋጠማቸው ዜጎች ተደራሽ የሆነ የጤና አገልግሎቶችን ማረጋገጥ።
- ለአረጋውያን፣ ለጎዳና ተዳዳሪ ህፃናት፣ ለህግ ታራሚዎች እንዲሁም ለተፈናቃይ ዜጎች ንቅናቄና ግንዛቤዎችን በመፍጠር ተደራሽ የሆነ የጤና አገልግሎቶች ማጠናከር።
ቡድኖች
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ በሁለት ቡድኖች የተዋቀረ ሲሆን ይህም፡-
- የሴቶች ቡድን
- የማህበራዊ ጉዳይ ቡድን
ዋና ዋና ተግባራትና ኃላፊነቶች
- ከክልልና ከተማ መስተዳድር ጤና ቢሮዎች፣ ከፌደራል ሆስፒታሎችና ኤጀንሲዎች የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ መዋቅሮች ጋር በመተባበር ተግባራትን ማከናወንና በየ3 ወሩ የምክክር ጉባኤ በማካሄድ፣
- የክልልና ለከተማ መስተዳደር ጤና ቢሮዎች እንዲሁም የፌዴራል ኤጀንሲዎችና ሆስፒታሎች የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይን አካቶ ትግበራ መዋቅሮችን ለማጠናከር ተከታታይ ድጋፍ፣ ክትትል በማድረግ ግብረ መልስ መስጠት፣
- የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚውን ስትራቴጂክ እና አመታዊ እቅድን ከመዋቅሮች፣ ከባለድርሻ አካላት እና ከአጋር ድርጅች ጋር በመተባበር በማዘጋጀት ወደ ታች ማውረድ፣
- ለጤና አገልግሎት ሰጭዎች በፆተዊ ጥቃት መካለከልና ምላሽ አሰጣጥ ላይ በሞጁል የተደገፈ እና ደረጃውን የጠበቀ ስልጠና መስጠት፣
- የሴቶችን፣ ህጻናትን፣ ወጣቶችን እና አካል ጉዳተኝነት ተኮር ጉዳዮችን በአግባቡ እንዲከታተሉ እና በተግባራቶች ውስጥ እንዲያካትቱ ለጤናው ዘርፍ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት፣
- የህፃናት ማቆያ እና የጡት ማጥቢት ማኮርነሮችን ማቋቋም እና ማጠናከር፣
- ፆታዊ ጥቃትን/ወሲባዊ ጥቃትን (GBV/SV) ለመከላከል እና አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ የአንድ መስኮት ማዕከላትን ማጠናከር እና ማስፋፋት
- ከህፃናት ጤና ጋር የተያያዙ መመሪያዎችን ማዘጋጀት፣
- ፆታን መሰረት ባደረገ ጥቃት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘዴን በመተግበር፤ ወሲባዊ ትንኮሳን ለመከላከል የሚያስችል የአሰራር ስርዓት መዘርጋት፣
- የጾታዊ ጥቃትን ለመከላከል እና አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ብሔራዊ ስትራቴጂክ እቅድ ማዘጋጀት፣
- ሴቶች ተወዳዳሪና እና አቅም ያላቸው እንዲሆኑ የማብቃት ስራዎችን መስራት፣
- ለአካል ጉዳተኞች ፍትሃዊ፣ አካታች እና ተመጣጣኝ የሆነ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ማረጋገጥ፤
- ከሚመለከተው የሚኒስቴር መስሪያ ቤት የስራ አስፈፃሚዎች ጋር ቅንጅት በመፍጠር ውስጣዊ አሰራርን ማጠናከር፣
- ከአጋር ድርጅቶች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ትብብር ማጠናከር;
- የጤናው ዘርፍ የሥርዓተ-ፆታ ኦዲት ማካሄድ፣
- በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የሥርዓተ-ፆታ ትንተና ማካሄድ፣
- ሴቶችን፣ ወጣቶችን እና አካል ጉዳተኞችን ለማበረታታትና ለማብቃት ጥናት እና ምርምር ማካሄድ፣
- የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ እና የመዋቅሮችን ተግባራት አፈፃጸምን በመከታተልና በመገምገም ትግበራው የሚያሻሽሉ አዳዲስ ስልቶችን ተፈፃሚ ማድረግ።