የጌትስ ፋውንዴሽን መስራችና ባለቤት ቢል ጌትስ ጋር ዉይይት ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋንን ተደረሽ ለማድረግ፣ ጤናን እና ስነ ምግብን፣ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ አሰጣጥ፣ አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን እና የኤስዲጂ ኢላማዎች ከግብ እንዲደርሱ ከቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ጋር ጠንካራ አጋርነት መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡
የጌትስ ፋውንዴሽን መስራችና ባለቤት ቢል ጌትስ ጋር በተደረገው ውይይት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን ሚኒስትሯ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
እ.ኤ.አ. ከ 2018 በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ኢትዮጵያን የጎበኙት ቢል ጌትስ ከጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ጋርም ዉይይት አድርገዋል።
በውይይቱም የመረጃ ጥራትን ማሻሻል፣ መረጃን ለምርምር እና ፖሊሲ መጠቀም እና የሀገር ውስጥ አቅምን ማጠናከር ላይ ያተኮረ ሲሆን መድረኩ የጤና መረጃ ባህል ለማዳበር እና ጠንክሮ መሥራትን ለማስረፅ እድል ፈጥሯል ተብሏል።