ዩኤስኤአይዲ( USAID) 156 የጅን ኤክስፕርት ማሽኖች ድጋፍ ለጤና ሚኒስቴር አድርጓል

  • Time to read less than 1 minute
USAID

ድጋፉ ሶስት ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጪ የተደረገበት ሲሆን የቲቢ ፈጣን ሞለኪውላር ምርመራ በማድረግ የቲቢ በሽታን በፍጥነት ለማግኘት የሚያስችል ቴን ከለርድ የጂን ኤክስፐርት ማሽኖች ድጋፍ መሆኑ ታውቋል፡፡ በድጋፍ የተገኙት የጂን ኤክስፐርት ማሽኖቹ በተለይ ለተጎጂ ክልሎች እና የቲቢ ስርጭት ላለባቸው አካባቢዎች ላይ ላሉ ጤና ተቋማት እንደሚተላለፉ ተገልጿል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ በድጋፉ የርክክብ ስነስርዓት ላይ እንደተናገሩት የጤና ሚኒስቴር የሳንባ ነቀርሳን ለማጥፋት አዲስ የ7 ዓመታት ስትራቴጂክ እቅድ ማዘጋጀቱንና ዩኤስኤአይዲ ኢትዮጵያ በአዲሱ ስትራቴጂክ ዕቅድ ውስጥ ቁልፍ ሚና እንደነበረው ጠቅሰው ለእቅዱ ስኬት መረጃን መሰረት ባደረገ፤ ውጤታማ በሆነ መንገድ መተግበርን ይጠይቃል ብሏል።

በዛሬው እለት በዩኤስኤአይዲ በኩል የተደረጉት 156 ቴን ከለር የጂን ኤክስፐርት ማሽኖች ድጋፍ ፈጣን የሞለኪውላር ቲቢ ምርመራዎች ላይ ያለውን የተደራሽነት ክፍተት ለማጥበብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ዶክተር ደረጀ አክለው ገልጸዋል። ድጋፉ ዩኤስኤአይዲ ቲቢን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ያሉት ዶክተር ደረጀ ድጋፉ ከዩኤስኤአይዲ በቀጥታ የተደረገው የጄኔክስፐርት ማሽኖች ድጋፍ አሁን ላይ 391 ያደረሰው ሲሆን ድጋፉ ዩኤስኤአይዲ በኢትዮጵያ የቲቢ ምርመራ ተደራሽነትን በማስፋት ትልቅ አጋር እንደሚደርጋት በንግግራቸው አስቀምጠዋል። ለዚህም የኢትዮጵያ መንግስት ጤና ሚኒስቴር ለአሜሪካ ህዝብ እና ለአሜሪካ መንግስት እንዲሁም ዩኤስኤአይዲ ላደረጉት በጎ እና ጠቃሚ ድጋፍ ምስጋናውን ያቀርባል ብለዋል።

የዩኤስኤአይዲ በቲቢ ላይ የሚሰጠው ድጋፍ የቲቢ ምርመራን በማስፋፋት ላይ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን መድሃኒት የተላመደ ቲቢ ወይም ለኤምዲአር-ቲቢ ህሙማን ህክምና እና እንክብካቤ የሚሰጡ ሆስፒታሎችን አቅም ለማጎልበት፣ ከፍተኛ ጥራት ያለው መድሃኒት የሚቋቋም የቲቢ ክብካቤ አገልግሎትን በማስፋፋት ኢንቬስትመንት ላይ ለዓመታት ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የአለርት ኮምሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ የሆኑት ዶክተር ሽመልስ ገዛኸኝ ሲሆኑ የአለርት ኮምሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በዘርፉ በቂ የህክምና ባለሞያዎች ያሉት ቢሆንም የግብአት ወስንነት ሆስፒታሉ ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ ህክምና ለሚያስፈልጋቸው አገልግሎት ለመስጠት እንቅፋት እንደሆነበት ጠቁመዋል። ዶክተር ሽመልስ ዩኤስኤ አይዲ እያደረገ ላለው ድጋፍ ሁሉ ያመሰገኑ ሲሆን የቲቢ በሽታን ለማከም ዘመናዊ የተሻሻሉህክምናዎች፣ቀዶህክምና ክፍልና እቃዎች፣ አልጋዎችና ሌሎች ድጋፎች ያስፈልጋሉ ብለዋል፡፡

የዩኤስኤአይዲ የኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተር ሚስተር ስኮት ሆክላንድር በበኩላቸው ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ከመቶ አመታት በላይ ግንኙነት ያላቸው አገራት መሆናቸውን አስታውሰው በተለይ የጤና ስርአቱን ለማጠናከር በተለያዩ የጤና ዘርፎች በአጋርነት እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። የአሜሪካ መንግስ የኢትዮጵያ የጤና ስርአት ለመደገፍ በየአመቱ ሁለት መቶ ሚልዮን ዶላር ኢንቨስት እንደሚደረግ የተለጸ ሲሆን የዚሁ አካል የሆነው ቲቢን ለማጥፋት የሚደረገውን ርብርብ ለማገዝ የቲቢ በሽታን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚደረገው ድጋፍ ቀጥሎ ዛሬ ላይ156 የጅን ኤክፐርት ማሽኖች ድጋፍ መደረጉን አስታውቀዋል። ድጋፉ ለታካሚዎች ከሚሠጠው ጠቀሜታ ባሻገር ለበሽታው መከላከል እና መቆጣጠር አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል።

ሚስተር ስኮት ሆክላንድር በአገሪቱ የሚደረገውን የቲቢ በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ስራዎች ላይ የበሽታውን ስርጭትና የሚያስከትለውን ሞት በመግታት ረገድ የመጣውን ለውጥ አድንቀው በዘርፉ አብሮ ለመስራት እየተደረገ ላለው ትብብር ምስጋና አቅርበዋል። በኢትዮጵያ ቲቢን ለማቆም ለሚደረገውን ርብርብ በዩኤስኤ አይዲ በኩል የሚያደርገው ድጋፍ እና አብሮነት እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

የመድሀኒት የተላመደ ቲቪ ህክምና ክፍል፣ የጽኑ ህክምና ክፍል እና ላብራቶሪ እንዲሁም የህክምና ባለሞያዎቹ የስልጠና ማእከል ጉብኝት የተደረገ ሲሆን የድጋፉ የርክክብ ስነስርአትም ተካሂዷል።