ዛሬ ጳጉሜ 1 የበጎ ፈቃደኝነት ቀን በማስመልከት በአራዳ ክፍለ ከተማ በሚኒሊክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ እና የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት የትምህርት ተቋማትን ፅዱና ውብ በማድረግ እንደዚሁም የተተከሉ ችግኞችን በማረም ፣ በመኮትኮት እና በመንከባከብ መርሃ ግብር ተጀምሯል።
በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
መርሀ ግብሩ ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትምህርት ተቋማት ለተማሪዎች ምቹ ፣ ፅዱ፣ ውብና ማራኪ እንዲሁም ሳቢ እንዲሆኑ እና ለመማር ማስተማሩ ሂደት ጉልህ ሚና እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚያስችል ነው።
ጳጉሜ 1 የበጎ ፈቃደኝነት ቀን በተለያዩ መርሀ ግብሮች የሚቀጥል ይሆናል።