ዛሬ በሎሜ ቶጎ የተጀመረዉ 72 ኛው የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት መድረክ ላይ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን እየተሳተፈ ይገኛል።
ይህ 72 ኛው የአፍሪከ አህጉር ከዓለም ጤና ድርጅት ስድስት የአህጉራዊ አስተዳደር አካላት አንዱ ሲሆን 47 አባል ሀገራት ያሉት የአፍሪካ ክልል ሀገራት የሚወክሉበት ኮሚቴ ነው፡፡
በመድረኩም የአፍርካ የአለም ጤና ንኡስ ኮሚቴዎች እባላት የሚሰየም ሲሆን እኤአ የ2022 የስራ እፈጻጸም እንዲሁም የአፍሪካ ማህበረሰብ ጤና አሁናዊና ቀጣይ ስትራቴጅክ ጉዳዮች ከአለማችን ማህበረሰብ ጤና ጋር ያለዉ አጠቃላይ ሁኔታ በመድረኩ ቀርበው ምክክርና ውይይት የሚደረግ ይሆናል።
መድረኩም ለቀጠይ 5 ቀናት በሎሜ ቶጎ የሚቀጥል ይሆናል።