የኮሪያ መንግስት በኮፍ /KoFIH / ግብረሰናይ ድርጅት እና ኤክዚም ባንክ በኩል ለጤና ሚኒስቴር የኮቪድ 19 የዲያግኖስቲክ ላብራቶሪ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ

  • Time to read less than 1 minute
The Korean government

በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙ የጤና ሚኒስቴር  ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የኮሪያ መንግሥት በተለያዩ ሥራዎች የጤና ሴክተሩን እንደሚያግዝ ተናግረው ይበልጥ በእናቶችና ህፃናት ጤና፣ በጤና መድህን አገልግሎት፣ የህክምና ባለሙያዎች ስልጠና፣ የህክምና ቁሳቁስ ጥገና እና ኮቪድ-19ን መከላከልና መቆጣጠር እንዲሁም የፅኑ ህሙማን ህክምና መሣሪያዎች ላይ ያደረጉትን ድጋፍ  አንስተዋል፡፡ 


የተደረገው ድጋፍ የኮቪድ-19ን ለመከላከልና ለመቆጣጠር  ጠቀሜታ  የጎላ  እንደሆነ ዶ/ር ሊያ ታደሰ  የተናገሩ ሲሆን ይህ ድጋፍ የሁለቱ ሃገራት ጥብቅ ግንኙነት ያሳያል ብለዋል፡፡


የኮፍ /KoFIH / ግብረ ሰናይ ድርጅት ፕሬዘዳንት ኘ/ር ቺያግ ዩፐ ኪም የኢትዮጵያ እና የደቡብ ኮሪያ ግንኙነት ረጅም አመታት ያስመዘገበ መሆኑን አውስተው የኮቪድ-19 የዲያግኖስቲክ ላብራቶሪ ቁሳቁሶችን ድጋፍ በተጨማሪ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ሥርዓት ማጠናከር ላይ በትኩረት  እንደሚሠሩ ተናግረዋል፡፡


የኮሪያ መንግስት እና በኮፍ /KoFIH / የጤና ሰርዓትን አንዲጠናከር ፤ የወረርሽን ዝግጅትና ምላሽ እና የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና አገልግሎት ማጠናከር እንዲሁም የስፔሻሊቲ እና ሰብ-ስፔሻሊት ህክምና ትምህርት ለኢትዮጵያዊያን እንዲያመቻቹ  ዶ/ር ሊያ ታደሰ ጠይቀዋል፡፡ 


የኮቪድ-19 የዲያግኖስቲክ ላብራቶሪ ቁሳቁስ ድጋፍ ርክክብ የተደረገ ሲሆን የኮሪያ መንግስት ላደረገው ድጋፍ የምስጋና ደብዳቤ በጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር  ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተበርክቷል፡፡