የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ተሻሽሎ የወጣው መመሪያ ቁጥር 882/2014

  • Time to read less than 1 minute
Dr. Lia Tadesse

 የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ተሻሽሎ የወጣው መመሪያ ቁጥር 882/2014 በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል፡፡


ባለፉት ሁለት አመታት በሃገራችን ኢትዮጵያ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር እና ለመግታት የተለያዩ መመሪያዎችንና ደንቦችን በማውጣት ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል፡፡ 


የኮቪድ-19 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ መመሪያ 30/2013፣ እና ተሻሽሎ የወጣዉና በስራ ላይ ያለዉ መመሪያ ቁጥር 803/2013 እንደ ወረርሽኙ ነባራዊ ሁኔታ ተግባራዊ የተደረጉ ሲሆን የበሽታው አሁናዊ የስርጭት ደረጃ እና ክትባት በስፋት መገኘት እና በአገራችን የክትባቱ አቅርቦት እና ስርጭት አበረታችና መንግስት በነፃ እየሰጠ ከመሆኑ አንፃር 25 ሚልዮን የህብረተስብ ክፍሎች የተከተቡ ሲሆን ይህም ቁጥር በሚናደረገዉ የተቀናጀ ርብርብ እንደሚጨምር ታሳቢ በማድረግ የነበሩትን የተወሰኑ ክልከላዎችና ግደታዎች በማላላት ወይም በማስቀረት ይበልጥ ዉጤታማ የሚሆን የጥንቃቄ እርምጃዎችንና ክትባትን ትኩረት የሚያደርግ አድስ መመሪያ ማዉጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ መመሪያ ቁጥር 882/2014 ወጥቷል፡፡


የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ተሻሽሎ የወጣ መመሪያ 882/2014 መሰረት በማድረግ ከዚህ በፊት ሲተገበሩ ከነበሩ የጥንቃቄ እርምጃዎች የቀጠሉና ማሻሻያ የተደረገባቸው እንዲሁም በመመሪያ 803/2013 ተጥለው የነበሩ እና ከፊል ማሻሻያ የተደረገባቸው ክልከላዎች በመመሪያ ተካተዋል፡፡


ተሻሽሎ የወጣው መመሪያ 882/2014 ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ:-

https://www.moh.gov.et/site/Directive_882_2014