የጤና ሚኒስቴር፣ የክልል የጤና ቢሮዎች እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች የጋራ መድረክ ተጀምሯል

  • Time to read less than 1 minute
JSC

በጋራ የውይይት መድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ እንደተናገሩት የጤናው ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮች የጋራ መድረኩ በዘርፉ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት አፈጻጸምን፣ ተግዳሮቶችን እና የተገኙ ልምዶችን በጋራ ለመገምገምና የቀጣይ  አቅጣጫ ላይ ለመግባባት ይረዳል፡፡ 


የተለያየ ግጭት ያለባቸውን ሁሉንም አካባቢዎች በአግባቡ በመዳሰስ እና ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያገኙ፣ በሆስፒታሎች እና በጤና ተቋማት አስፈላጊ ግብዓቶችን በማሟላት የተቋረጡ የሕክምና አገልግሎቶች መልሰው እንዲጀምሩ ማድረግ እንደሚገባ የገለፁት ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ይህም በጋራ የውይይት መድረኩ በትኩረት የሚገመገም አጀንዳ አንዱ መሆኑን አስረድተዋል፡፡


የሴክተሩ የስድስት ወር የስራ አፈጻጸም፣ የጤና ዘርፍ የፋይናንስ ስርአትና የፕሮግራሞች አፈጻጸምን የተመለከቱ ሪፖርቶች የቀረቡ ሲሆን ከጤና ሚኒስቴር፣ ከፌደራል እና በክልል በየደረጃው ካሉ የሥራ አመራሮች የተገኙ ሲሆን  በቀረበው ሪፖርት ላይም ትኩረት የሚሹ የውይይት ነጥቦች ተንስቶ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡


ውይይቱምን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እየመሩ ሲሆን የክልል ጤና ቢሮ እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች  እየተሳተፉ ነው፡፡