የጤና ሚኒስቴር በአለታ ወንዶ ከተማ በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ አባወራዎች ያስገነባቸው  ቤቶችን ለተጠቃሚዎች አስረከበ 

  • Time to read less than 1 minute
Aleta Wondo

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በክረምት በጎ አገልግሎት በአለታ ወንዶ ከተማ በዝቅተኛ ኑሮ ለሚገኙ ስድስት አባወራዎች/እማወራዎች ያስገነባቸውን ቤቶች ለተጠቃሚዎች ያስረከቡ ሲሆን በክረምት በጎ አገልግሎት የጤና ሚኒስቴር ችግኞችን የመትከል እና አቅመ ደካሞችን የማገዝ ስራን ሲሰራ እንደነበር አስታውሰው በአለታ ወንዶ ከተማም ምሳሌ መሆን የሚችል ስራ መሰራቱን ተናግረዋል። ቤቶቹም መሰረታዊ መገልገያ ቁሳቁስ የተሟላላቸው ሲሆን ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። 


ድጋፍ የተደረገላቸው ግለሰቦችም በሰጡት አስተያየት መጠለያ ማጣት እጅግ አስቸጋሪ ህይወት እንዲመሩ እንደዳረጋቸው ሆኖም ጤና ሚኒስቴር  እንደደረሰላቸው እና ተስፋቸውን እንዳለመለመ ገልጸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል። 


በተያያዘም  በጉብኝታቸው የአለታ ወንዶ ሆስፒታልን ጨምሮ በጤና ጣቢያ እና በትምህርት ቤት በመገኘት ትኩረት የሚሹ ሀሩራማ በሽታዎችን ለመከላከል የተሰሩ ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። የጤና ተቋማቱ የሀሩራማ በሽታዎችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በተለይ በግል እና በአካባቢ ንጽህና አጠባበቅ ፣በሀሩራማ በሽታዎች ህክምና እና ማገገም ዙሪያ አበረታች ስራ መስራታቸውን ገልጸዋል። ስራዎቹ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።