አዳዲስ ምሩቃን ሃኪሞችን ወጪን በመጋራት  ወደ ስራ ለማስገባት ከጥቂት ሳምንታት በፊት ይፋ የተደረገውን ፕሮጀክት አስመልክቶ ምክክር ተደርገ

  • Time to read less than 1 minute
HR

ጤና ተቋማት ያለባቸውን የሰው ሃይል እጥረት ለማቃለል እና ለተመራቂ ሃኪሞች የስራ እድል ለመፍጠር ይፋ የተደረገውን የ3 ዓመት ፕሮጀክት ስራ በተመለከተ ወርክሾፕ ተካሂደዋል።


ጤና ሚኒስቴር ከአጋር ድርጅቶች እና ክልል ጤና ቢሮዎች ጋር በመሆን ወጪን  በመጋራት አዳዲስ ሃኪሞችን ወደ ስራ ለማስገባት በተጀመረው ፕሮጀክት መሰረት እየሰራ መሆኑን የተናገሩት በጤና ሚኒስቴር የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ደምሴ በፕሮጀክቱ ከ2011 ጀምሮ ተመርቀው ያልተቀጠሩ 2898 ሃኪሞችን ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችል የበጀት ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጸዋል፡፡


ከክልል ርዕስ መስተዳድር ቢሮ፣ ከከተማ አስተዳደር፣ ከክልልና ከከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮና ፋይናንስ ቢሮ እንዲሁም ከጤና ሚኒስቴር እና አጋር ድርጅቶች የተውጣጡ ተሳታፊዎች በተገኙበት ወርክሾፕ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች  የክልላቸውንና የከተማቸውን ተጨባጭ ሁኔታ በማገናዘብ ፕሮጀክቱ እውን የሚያደርጉበትን መንገድ በተመለከተ ውይይት ተደርጓል። በወርክሾፑ ላይ የክልልና የከተማ አስተዳደር ተወካዮች በበኩላቸው ፕሮጀክቱ ይፋ ከተደረገበት እስከ አሁን የሰሯቸውን የዝግጅት ስራዎች አቅርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን በቀጣይም በጋራ ለማሰራት የሚያስችል የድርጊት መርሐ ግብር ተዘጋጅቶ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ወደ ቅጥር ስራ የሚገባ ይሆናል።


ይህ ፕሮጀክት ከክልል እና ከተማ አስተዳድደር ጤና ቢሮዎች ጋር በመሆን ታህሳስ 21፣2014 ዓም  በይፋ የተጀመረ ሲሆን ይህንንም አስመልክቶ በጤና ሚኒስቴር እና የክልል እንዲሁም የከተማ አስተዳድደር ጤና ቢሮዎች መካከል የመግባቢያ ሰነድ በዚያ ዕለት መፈረሙ ይታወሳል፡፡