ራዕይ
ሚኒስትር መ/ቤቱ እና የክልል ጤና ቢሮዎች ወረቀት አልባ የቴክኖሎጂ ስርዓትን በመጠቀም የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራታቸውን ቀልጣፋ እና ዘመናዊ እንዲሆን ማድረግ።
ተልዕኮ
ሚኒስትር መ/ቤቱ እና የክልል ጤና ቢሮዎች የውስጥ አሰራራቸውን በዘመናዊ እና ቀልጣፋ በሆነ ዲጅታል ቴክኖሎጂ ስርዓት እንዲጠቀሙ በማድረግ የ አይ ሲ ቲ በመሠረተ ልማት አቅምን ማሳደግ ፤ ማሻሻል እና የ ዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክህሎታቸውም የዳበረ እና የበቃ እንዲሆኑ ማስቻል።
ዓላማ
በሚ/ር መ/ቤቱ የአይ ሲ ቲ ሥራዎችን በመምራት እና በማስተባበር ፣ የመረጃ ስርዓቶች (ዲጂታል ቴክኖሎጂ ስርዓቶች) እንዲለሙ ማድረግ፣ አፈጻጸማቸውን መከታተል ፤ መገምገም ፤ የመረጃ አውታር (ኔትዎርክ) በማሻሻል እና በማዘመን የተቋሙን የውስጥ አሰራርን ዘመናዊ እና ቀልጣፋ እንዲሆን ማድረግ፤፤
እሴቶች
- የ ሚ/ር መ/ቤቱ የውስጥ ሠራተኞች፤ የ ክልል ጤና ቢሮ ሠራተኞች እንዲሁም አጠቃላይ ማህበረሰባችን ትልቁ ሀብቶቻችን እና የጤናው ዘርፍ አገልጋዬች በመሆናቸው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ስርዓት እና አጠቃቀም ላይ ቅድምያ በመስጠት ማገልገል፤፤
- በሁሉም ስራዎቻችን ላይ የላቀ አገልግሎትን፣ ታማኝነትን፣ ጨዋነትን የተላበሱና ብቃትን መሠረት አገልግሎት አሰጣጥን ማለጋገጥ፤፤
- ስራዎቻችንን በታማኝነት፣ በሙያዊ ብቃት፣ በአክብሮት፣ በስርዓት፣ በተጠያቂነት እና ተቋማዊ ቁርጠኝነትን በተላበሰ መንገድ መከናወናቸውን መከታተል፤፤
የኢንፎርሜሽን ኮምኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሥራ አስፈጻሚ ተግባርና ኃላፊነት
- የሀገሪቱን የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ስትራቴጂ መሰረት በማድረግ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ተልዕኮ ጋር የተጣጣመ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ስትራቴጂ፣ ዲጂታል ስትራቴጂ እና መሪ ፕላን ያዘጋጃል።
- በሚኒስቴር መ/ቤቱ የስራ አካባቢ የቴክኖሎጂ አገልግሎቶችን እና የመፍትሄ ሃሳቦችን ማስፋፋት እና ከሚ/ር መስሪያ ቤቱ ውጭ ካሉ ሌሎች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማቶች ጋር ያለውን ግንኙነት ያጠናክራል።
- የሚኒስቴር መ/ቤቱንና የክልል ጤና ቢሮ ሠራተኞችን የዲጂታል ክህሎት ክፍተትን በመለየት መሙላትና በመረጃ ልውውጥ አቅም ማሳደ።
- የሚኒስቴር መ/ቤቱን ኢሜይል ማስተዳደር፣ ድረ-ገጽ እና ማህበራዊ ሚዲያ ሰራተኞች የቴክኒካል ድጋፍ መስጠትና አዳዲስ አሰራሮችን በመተግበር ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃዎችን በትክክል እየደረሰ መሆኑን ማረጋገጥና ክትትል ማድረግ።
- አዳዲስና ነባር የቴክኖሎጂ መረጃ ስርዓቶችን ለማስተናገድ በሚያስችል መልኩ በሚኒስቴር መ/ቤቱ ውስጥ ያለውን የአይ ሲ ቲ መሠረተ ልማት የማጠናከርና የማሻሻል ስራ ይሰራል።
- የአይ ሲ ቲ ፖሊሲና መመሪያዎችን ማዘጋጀት እና መተግበር እንዲሁም የአይ ሲ ቲ ግብዓቶችን በተመለከተ አጠቃቀምን፣ ግዥ እና አወጋገድ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን መመሪያዎችን ያዘጋጃል፤፤
- በሚ/ር መ/ቤቱ ቀልጣፋ የመረጃ ልውውጥና የተሻሻለ አሰራር እንዲኖር የኔትዎርክ መሠረተ ልማት ዝርጋታን ይቆጣጠራል ፣ በትክክልና በተገቢው መሰራቱን ያረጋግጣል።
- ደህንነቱ የተጠበቀ ፣ አስተማማኝ እና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት የአይ ሲ ቲ መሠረተ ልማቶችን ፣ ግብዓቶችን እና መተግበሪያዎችን ያስተዳድራል ይቆጣጠራል።
- በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የተደራጀና ዘመናዊ የደህንነት ቴክኒኮችን እና ሶፍትዌሮችን በመተግበር ውስጣዊና ውጫዊ የሳይበር ደህንነት ስጋትንና ይቆጣጠራል።
- የሚ/ር መ/ቤቱን የመረጃ ማዕከል ማጠናከር ፣ ማሻሻል እና ማስተዳደር ፣ ደህንነቱን መጠበቅ ፣ አስተማማኝ እና አመቺ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎቶችንና የመፍትሄ ሃሳቦችን ማቀረብና ስርዓቶችን መዘርጋት እንዲሁም አስተማማኝ የአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ መረጃዎችን ይይዛል በአደጋ ጊዜም ፈጣን ምላሽ ይሰጣል።
- የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞችን የአይሲቲ አገልግሎቶችን ሲጠቀሙ የክህሎት ክፍተት ይለያል ፣ ስልጠና እንዲሰጥ ያመቻቻል ፤ ያስተባብራል እንዲሁም የአይ ሲ ቲ ግብዓቶችን እና አዳዲስ መተግበሪያዎችን የአጠቃቀም ላይ ግንዛቤ ይፈጥራል።
- የሚ/ር መ/ቤቱን የመረጃ ስርዓት ፍላጎት በጥናት እንዲለዩ ያደርጋል ፣ ይገመግማል
- በጥናት የተለዩት የመረጃ ስርዓት ፍላጎቶችን መሰረት በማድረግ የሶፍትዌር ልማት ዋና ዋና ምዕራፍ/ ተግባራትን ማለትም የስርዓት ትንተናና ዲዛይን ፣ ፕሮግራም ኮዲንግ ፣ የፕሮግራም ትክክለኛነት ፍተሻ እንዲደረግ በማድረግ የሶፍትዌር ልማት ስራ ይሰራል ፣ በጥራት እንዲከናወን ያስተባብራል፣ ይከታተላል፣ የለሙትንም ይገመግምል።
- በሚለሙት ሶፍትዌሮች ዙሪያ የስልጠናና የአጠቃቀም መመሪያዎችን/ማኑዋሎቸን እንዲዘጋጁና ለሚመለከታቸው አካላት ስልጠና ይሰጣል ፣ እንዲሰጥ ያስተባብራል።
- እንዲለሙ የተደረጉት ሶፍትዌሮች በተቋሙ እንዲተገበሩ እና ቀጣይነት ባለው መልኩ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል።
- የአይ ሲቲ እቃዎች እና አገልግሎቶችን ግዥ የሚያደርጉ የሚኒስቴር መ/ቤቱ የስራ ክፍሎችን ይደግፋል።
- ከአይሲቲ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ የመ/ቤቱን ሰራተኞችና ከፍተኛ አመራሮችን የማማከር አገልግሎት ይሰጣል።