የፖሊሲና ስትራቴጂ ጥናትና ምርምር መሪ ስራ አስፈፃሚ

የሥራ ክፍሉ ዓላማ

  • የጤናውን ዘርፍ የጥናትና ምርምር ሥራዎች በማቀድ ማስተባበር እና መምራት ምርምር ውጤቶች ለፖሊሲ ግብዓትነት እንዲውሉ ማስቻል እና የፖሊሲዎች ናስትራቴጂዎች ቀረፃ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን በማድረግ ዘርፉ ያስቀመጣቸውን ግቦች ማሳካት ነው፡፡

ራዕይ

  • ፖሊሲ እና አሰራርን የሚያሻሽል መረጃ በማመንጨት፤ በመተርጎም እና ለውሳኔ እንዲውል በማድረግ የኢትዮጵያ ህዝብ ጤናው ተጠብቆ ማየት

ተልዕኮ

  • በኢትዮጵያ የጤና ስርዓት ውስጥ በመረጃ ላይ የተደገፈ ውሳኔ አሰጣጥን ማጎልበት እና ባህል እንዲሆን ማስቻል

የስራ ክፍሉ ኃላፊነት

የፖሊሲና ስትራቴጂ ጥናትና ምርምር የስራ ክፍል በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የፀደቁ ሰባት የሚጠበቁ ውጤቶች ያሉት ሲሆን የስራ ክፍሉ የሚከተሉት ስራዎች በኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡

  • የዘርፉን የፖሊሲና ስትራቴጂ ጥናትና ምርምር ሥራዎች ማቀድ፣ማስተባበር፣መምራት
  • ለዘርፉ ፖሊሲ፣ ስትራቴ ጥናት እና ምርም የሚያግዙ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት፣ ማሻሻል
  • የዘርፉን ችግሮች ለመፍታት የሚያግዙ የትንተና እና ትንበያ ስራዎችን ማስተባበር፣ መምራት
  • የዘርፉን ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ቀረፃን በበላይነት መምራት፣ እንዲፀድቁ መከታተል፣ የፖሊሲ ክትትል እና ግምገማ ሥራዎችን ማስተባበር
  • በዘርፉ የፖሊሲ ጥናት እና ምርምር ሥራዎችን ማስተባበር የምርምር አጀንዳ እንዲቀረጽ ማድረግ፣ መከታተል፣ መገምገም
  • የአስቸኳይ ጊዜ አደጋዎች ምላሽ እና የመልሶ ማቋቋም ሥራዎች በበላይነት መከታተል፣ ማስተባበር
  • በዘርፉ የተዘጋጁ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጅዎች፣ የጥናት እና ምርምር ውጤቶች በዘመናዊ ዳታ ቤዝ እንዲደራጁና እንዲተዋወቁ ማድረግ፣ ማስተባበር