የጤና ዘርፍ የሰው ሃብት ልማትና ማሻሻያ መሪ ስራ አስፈጻሚ

Human resource development

ራእይ፦ ብቃት ያላቸው፣ ተነሳሽ የሆኑበቂ ቁጥር እና ሩህሩህ የጤና ባለሙያዎች እንዲፈሩ ማድረግ

የስራ ክፍሉ ስትራተጂክ በሆነ መንገድ ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች የጤና ባለሙያዎች ከሀገሪቱ የጤናና የህዝብ ቁጥር ፍላጎት አንጻር ብቃትን የተለባሱ እና እውቀታቸው በተከታታይነት እንዲያድግ ፤ ከህዝብ ጥመርታ አንጻር ተመጣጣኝ ቁጥር መኖሩን ማረጋገጥ፤ የጤናው ዘርፍ ሰራተኞች ሁለንተናው የጤና አገልግሎትን እንዲያረጋግጡ እና ፍትሀዊ ተደራሽነትን ለማስፈን ተነሳሽነታቸው እንዲጨምር፤ ከፍተኛ አፈጻጸም እንዲኖራቸው ትኩረት ይደረጋል

​​​​​​​የመሪ ስራ አስፈሚው ሃላፊነትና ተግባር

  • ለጤና ሴክተሩ የሚፈለገውን የሰው ሃይል ብዛት እና አይነት መወሰን
  • የጤና ባለሙያዎችን ብቃት አሃድ፣ ሥርዓተ ትምህርት እና የተግባር (ስራ) ወሰን መወሰን
  • ለጤናው ዘርፍ የሚኣስፈልጉ አዳዲስ የሙያና ስራ ዓይነቶች መቅረጽ 
  • የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞችን እና ሌሎች የመካከለኛ ደረጃ ስልጠናዎችን መደገፍ
  • በእውቀት እና ፍላጎት ላይ የተመሰረተ የጤና ሙያ ምርጫ  ስርኣት ማጠናከር
  • የብሄራዊ የህክምና ስፔሻሊቲ ፕሮግራም (ERMP) መምራት ማስተባበር
  • የሴት የጤና ባለሙያዎችን ተዋጽዎ በሕክምና፣ በሕክምና ስፔሻሊቲ ቁጥር እንዲጨምር ማስተባበር
  • የህብረተሰብ ጤና ስልጠና፣ የፊልድ ኤፒዲሚዮሎጂ ስልጠና ፕሮግራም እና ሌሎች በፍላጎት ላይ የተመሰረተ የስልጠና መርሃ ግብሮችን መምራት
  • የጤና ሳይንስ ትምህርት እና ስልጠና ጥራትን መደገፍ እና ማጠናከር
  • በጤና ሳይንስና የሥልጠና ተቋሞችን የትምህርት መርጃዎች አስፈላጊ የክህሎት ላብራቶሪ ቁሳቁሶችን መደገፍ
  • የነርሲንግ ስፔሻሊቲ እና ከህምና ስፔሻሊቲ ጋር በቡድን የሚሰሩ ባለሙያዎች ማፍራት
  • የዲጂታል ጤና ትምህርት ቴክኖሎጂዎችን ማጠናከር እና መደገፍ
  • በሁሉም የመንግስት እና የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የጤና ሳይንስ ትምህርት ማጎልበቻ ማእከላትን መደገ
  • ተከታታይነት ያለው የሙያ ማጎልበቻ (CPD) ተደራሽነት እና ቁጥጥርን ማረጋገጥ
  • የተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ እውቅና ሰጪዎችን እና አቅራቢዎችን ቁጥር ማስፋፋት
  • ለጤናው ዘርፍ ሰራተኞች የተለያዩ አቅም ግንባት ስልቶችን መቅረጽና ማስተባበር
  • የጤና ሰራተኞች ማትጊያና ማበረታቻ ዘዴን ማጠናከር እና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ
  • ጤና የሰው ሃይል መረጃ ማቅረብ፤  የጤና የሰው ሃይል ትንበያ፣ እቅድ እና ልማት መምራትና መስተባበር
  • የተቀናጀ የሰው ሃብት መረጃ ስርዓት (iHRIS) ማስተባበር
  • የብሔራዊ ጤና የሰው ኃይል መለያዎች (NHWAs) አተገባበርን ማጠናከር
  • ለክልል ጤና ቢሮዎች፤ ለተቀሟት፤ ለግል ድርጅቶች ድጋፍና ክትትል ማድረግ
  • ከሙያ ማህበራት እና ከ ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር መስራት
  • ከሀገር አቀፍ እና አለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በትብብር መስራት