ራዕይ፤
ጤናማ፣ ውጤታማ እና የበለጸገ ማህበረሰብ ማየት
ተዕልኮ፤
የማህበረሰቡን ጤና እና ደህንነት ለማሳደግ ከፍተኛ ጥራት ያለው፣ ምላሽ ሰጪ እና ተጠያቂነት የሚያረጋግጥ የጤና ስርዓት እዉን በማድረግ የሚፈለገዉን የጤና ውጤት ማምጣት፣ ማሀበረሰቡ በጤና ስርዓቱ ላይ መተማመን ማሳደግ ብሎም የህብረተሰብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማጎልበት
አላማ:
ባለድርሻ አካላትን በማስተባበርና ቅንጅታዊ አሰራር በመፍጠር፣ የፓሊሲ ሃሳቦችን በማመንጨት፣ አድቮኬሲ ስራዎችን በማካሄድ፣ የአመራር የማስፈፀም አቅምን በማሻሻል፣ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ፣ የጤና ስረዓትን ለማሻሻል የሚረዱ የፈጠራ ስራዎችን በማከናወን አዳዲስ ቴክኖሎጅዎችን በመለየት፣ በማበልፀግና ተግበራዊ በማድረግ፣ የጤና ስርዓት ጥራትና እና የጤና አገልግሎት ፍትሃዊ ተደራሽነትን ማረጋገጥ ነው፡፡]
በመሪ አስፈፃሚው ስር ያሉ ዴስኮችን በማስተባበር እና በማቀናጀት የዕቅድ ዝግጅት፣ ትግበራ፣ ክትትልና የመማማር ስራዎችን ያከናዉናል፡፡
- የተቋሙን ስትራቴጂክ ዕቅድ መሰረት በማድረግ የዋና ሥራ አስፈጻሚ ሥራ ክፍልን አመታዊ ዕቅድና በጀት ያዘጋጃል፤ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣ ሲጸድቅ ለዴስኮቹ ያስተዋውቃል፣ በሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል ይገመግማል፡፡የዴስኮቹን የሥራ አፈጻጸም ይገመግማል፡፡
- በሚያስተባብራቸው ዴስክ ኃላፊዎችን የአቅም ክፍተት በመለየት አቅማቸው እንዲገነባ ልዩ ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡
- የሚያስተባብራቸውን ዴስክችን የአፈጻጸም ጥንካሬና ድክመት በክትትልና ግምገማ በመፈተሸና በማጥናት ዘመናዊና ቀልጣፋና የአሰራር ሥርዓት ይዘረጋል፡፡
- በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ተሞክሮ በመቀመር አዳዲስ የአሰራር ዘዴዎችና የአሰራር ስልት ይቀይሳል፣ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
- በዴስክች መካከል ቅንጅታዊ አሠራር በመዘርጋት መልካም ተሞክሮ እንዲቀመር በማድረግ እንዲሰፋፉ ያደርጋል፡፡
- በሚያስተባብራቸው ዴስኮች በሚሰጡ አግልግሎቶች የተገልጋዮች እርካታ ዳሰሳ ጥናት እንዲካሄድ ያደርጋል፣ በሚገኘው ግብረመልስ መሰረት አሰራሩን ያሻሽላል፣ ተግባር ላይ እንዲውል ያደርጋል፡፡
- በአገልግሎት አሰጣጥ የሚስተዋሉ የአሰራር ችግሮች በክትትልና ድጋፍ በመለየት የአሰራር ማሻሻያ ይዘረጋል፣ ተግባራዊነቱንም ያረጋግጣል፣ ማሻሻያ ያደርጋል፡፡
በተቋሙ የሥራ አመራር ኮሚቴ ይሳተፋል፤እስትራቴጂያዊ በሆኑ ጉዳዮች የጋራ ውሳኔ እና የምክር አገልግሎት ይሰጣል፤
- በተቋሙ የሥራ አመራር ኮሚቴ በሚደረገው ስብሰባበ መሳተፍ የፕሮጀክቶችን አፈጻጸም ይገመግማል፡፡
- የተቋሙን ስተራቴጂክ ዕቅድ በጋራ ያዘጋጃል፣ ይገመግማል፣ በጋራ ያጸድቃል፡፡
- የተቋሙ ዕቅድ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤትና በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሲገመገም በግምገማው ላይ ይሳተፋል፣ ቴክኒካል ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ይሰጣል፡፡
- በተቋሙ በሰው ሀብት ሥራ አመራር ዘርፍ የሚዘጋጁ አዋጆች ደንቦች እና መመሪያዎችን ገምግሞ ለሚመለከታቸው አካላት ለውሳኔ ያቀርባል፡፡
- በሥራ ላይ ባሉ ደንቦችና መመሪያዎች ላይ ለየት ያሉና የከፍተኛ ኃላፊዎችን ውሳኔ የሚሹ ጉዳዮች ሲቀርቡ ህጉንና አሠራሩን በማገናዘብ የውሳኔ አስተያየት ለከፍተኛ አመራሩ ያቀርባል፡፡
- የተቋሙን አሠራር ውጤታማና ቀልጣፋ ሊያደርጉ የሚችሉ አዳዲስ አሰራሮችን መዘርጋት የሚያስችል ሀሳብ ያፈልቃል፡፡
የጤና ስርዓት ጥራት፣ ፍትሃዊነትና ተደራሽነትን ማሻሻል
- የጤና ስርዓትና አገልግሎት ጥራትን፣ ፍትሃዊነትና ተደራሽነትን ለማሻሻል የሚረዱ ፖሊሲዎችን ስትራቴጅዎችን፣ መመሪያዎችና ፕሮቶኮሎችና ፓኬጆች እንዲዘጋጁ ያስተባብራል፡፡
- ባለድረርሻ አካላትን በማስተበባርና በመምራት የጤናው ዘርፍ የትግበራ ማዕቀፎች ጥራታቸውን የጠበቁ፣ ፍትሃዊነትና ተደራሽነትን የሚያረጋጡ እንዲሆኑ ይደግፋል፣ ያስተባብራል፣ ይከታተላል፡፡
- አዳዲስ የሀገር አቀፍ የጤና ስረዓት ማሻሻያ ኢኒሸትቮችን እንዲቀረፁ ያድርጋል፣ ቴክኖሎጅዎችንና ፈጠራዎች እንዲለዩ እንዲበለፅጉ በማድረግ ተግበራዊነቱን ይከታተላል፡፡
- አዋጪ፣ ውጤታማ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ ያልሆኑ የስራ ሂደቶች እንዲለዩ ያደርጋል፣ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፡፡
- የተለዩ ጥራትና ፍትሃዊነት ማስጠበቂያ ኢኒሸቲቮች፣ ቴክኖሎጅዎች፣ ፈጠራዎች እና አሰራሮችን የሙከራ ትግበራን ይመራል፣ የሙከራ ትግበራውን ሲያልፍ ተግበራዊ መደረጉን ያረጋግጣል፡፡
- ከሚመለከታቸው ባድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በየደረጃው የጤና ስርዓት ማሻሻያ የስትሪንግ፣ የአማካሪና የቴክኒካል ኮሚቴዎችን እንዲቋቋሙ ያደርጋል፡፡
- የጤና ስርዓት ጥራት፣ ፍትሃዊ ተደራሽነትን ለማሻሻል የሚረዱ መልካም ተሞክሮዎች እንዲለዩ እንዲቀመሩና እንድስፋፉ ይደግፋል፡፡
- የጤና ተቋማት የጥራት ማረጋገጫ (Accreditation) ስርዓት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እንዲዘረጋ ያደርጋል፣ የጤና ተቋማት የጥራት ማረጋገጫ መስፈርቱን እንዲያሟሉ ይደግፋል፡፡
- የጤና አገልገሎት ጥራትን ለመለካት የሚያስችሉ አመላካች መስፈርቶችና ዳሽቦርዶችን እንዲዘጋጁ በማድረግ በየጊዘው መረጃዎች መለካታቸውንና መተንተናቸውን ያረጋግጣል፡፡
የፓሊሲ ሃሳቦችን ያመነጫል ፤ የአድቮኬሲ ስራዎች ያከናውናል፤
- የጤና ስርዓት ጥራት፣ ፍትሃዊ ተደራሽነትን ዙሪያ የፖሊሲና የጥናት ሃሳቦችን በማመንጨት ጥናት እንዲካሄድ አመራር ይሰጣል፣ አቅጣጫ ያሰቀምጣል፣ የጥናት ውጤቶችን ያዳብራል ዉጤቱንም ለዉሳኔ ይጠቀማል፡፡
- ከመንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ አጋር ድርጅቶች ጋር ለሚሠሩ ሥራዎች አስፈላጊ የሆኑ አጋሮች እንዲለዩ ያደርጋል፣ በጋራም ውይይቶች ያካሂዳል፣ ይወስናል፣ በሀገር ዉስጥም ሆነ በውጭ ሃገር የልምድ ልውዉጥና ኮንፈረንስ ላይ ይሳተፋል፣ የዴስክ ሃላፊዎችም እንዳስፈላጊነቱ እንዲሳተፉ ያደርጋል፡፡
- የጤና ስርዓት ጥራት፣ ፍትሃዊ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ አጋር ድርጅቶች ጋር በሚደረጉ ስምምነቶች የተዘጋጁ የመግባቢያ ሰነዶችን ያጸድቃል፣ ይፈራረማል፣ ሃብት ለማሰባሰብ የሚያግዝ ኘሮፓዛል እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ የተዘጋጁ ኘሮፓዛሎችን ትክክለኛነታቸውን ያረጋግጣል የማስተካከያ እርምጃወችንም ይወስዳል፡፡
- የአድቮኬሲ ስራ የሚያስፈልጋቸዉ የጤና ስርዓት ጥራት፣ ፍትሃዊ ተደራሽነትን የሚመለከቱ ጉዳዮችን በመለየት የከፍተኛ ደረጃ አድቮኬሲ ያካሂዳል፣ የመጣዉን ለዉጥም ይከታተላል፡፡
- በመገናኛ ብዙሃን የሚተላለፉ የጤና ስርዓት ጥራት፣ ፍትሃዊ ተደራሽነትን የሚመለከቱ አጫጭር መልእክቶች እንዲዘጋጁ አመራር ይሰጣል፣ ይከታተላል፣ በመጨረሻም ለህብረተሰቡ መድረሳቸዉን ክትትል እንዲካሄድ ያደርጋል፡፡
- እንደ ግንዛቤ ደረጃው ለሕብረተሰቡ የአድቮኬሲ፣ የግንዛቤ ማስጨበጫና የማሕበረሰብ ንቅናቄ ስራ እንዲሰራ አመራር ይሰጣል፣ይገመግማል፡፡
ክትትልና ድጋፍ ማድረግ የማስፈፀም አቅምን ያሻሽላል፡፡
- በየደረጃው የሚደረጉ የድጋፍና ክትትል ስራዎችን ያስተባብራል፣ ይመራል፡፡
- በድጋፍና ክትትል የተለዩ ክፍተቶች ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የተሰጠው ግብረ-መልስ ተፈፃሚ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡
- ጥራትንና ፍትሃዊ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚረዱ አዳዲስ ፕሮጀክቶች እንዲቀረፁና እንዲተገበሩ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፣ አመራር ይሰጣል፡፡
- የጤና ስርዓት ጥራትና ፍትሃዊ ተደራሽነትን በተመለከተ የአቅም ክፍተት እንዲለይ ያደርጋል፣
- በተለየው ክፍተት መሰረት የስልጠና ማንዋልና የተለያዩ ሰነዶች ዝግጅት ሂደት ላይ አመራር ይሰጣል፣ እንዳስፈላጊነቱ ትክክልነታቸዉን በማረጋገጥ በሥራ ላይ ስልጠናና ተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ዴስክ በኩል ክሬዲት እንዲሰጣቸዉ በማድረግ ያጸድቃል፡፡
- የጤና ስርዓት ጥራትን ለማስጠበቅ የሚረዱ የተለያዩ ስልጠናዎች እንዲሰጥ ያደርጋል፣ የጥራት ባህል እንድዳብር ያደርጋል፡፡
- ተመጣጣኝ ድጋፍ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችና አካባቢዎች የቴክኒክ፣ ፋይናንስ፣ ግብዓትና መሰረተ ልማት ፍላጎቶችን እንዲለይና ድጋፍ እንዲደረግ ያደርጋል፡፡
- የጤና ስርዓት የጥራትና ፍትሃዊ ተደራሽነትን ማስጠበቂያ ፅንሰ ሃሳቦች በጤና ስርዓት የትግበራ ማዕቀፎች
- ውስጥ እንዲካተቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራት እንዲከናወኑ ያደርጋል፡፡
የአመራር የማስፈፀም አቅምን ያሻሽላል፡፡
- የጤናውን ዘርፍ አመራር ክፍተት መለያ መስፈርቶችን እንዲዘጋጁና የክህሎትና ብቃት ክፍተት እንዲለዩ ያደርጋል፡፡
- የአመራርነት ዝንባሌና ፍላጎት ያላቸውን ተተኪ ባለሙያዎችን በመለየት የስራ ላይ ክትትልና እንዲደረግ ያስተባብራል፡፡
- በጤናው ዘርፍ በየደረጃው የአመራር ተጠያቂነት ለመዘርጋት የሚረዱ ስትራቴጅዎችን እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፡፡
- በየደረጃው ያለው የጤናው ዘርፍ ብቃት ያለው ተተኪ አመራር ለማፍራት የሚያስችል መስፈርትና መመሪያ እንዲዘጋጅና እንዲተገበር ያደርጋል፡፡
- ተመጣጣኝ ልማት በሚሹ አከባቢዎችን በመለየትና ትኩረት በመስጠት የአመራር ብቃት እንዲሻሻል አስፈላጊውንድጋፍ ያደርጋል፡፡
ወረርሽኝና ድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎችን የመከላከል፣ የመቆጣጠር እና ምላሽ የመስጠት ስራዎችን ያክርናውናል፤
- የህብረተሰብ ወረርሽንና ድንገተኛ አደጋ ሲከሰት (Mass causality) በቦታው በመገኘት የህክምና ዕርታዳታ እና የጤና ምክር ይሰጣል፡፡
- ሕብረተሰብ አቀፍ ወረርሽና የድንገጠኛ አደጋዎች ላይ ቅኝትና ምላሽ ላይ በመሳተፍ ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ ጤና ስራ አመራር
- የማህበረሰብ ንቅናቄ ውይይት ያካሂዳል፣ ማህበረሰቡን ያስተባብራል፣ የማህበረሰብ ባሌቤትንነትን ያጎለብታል፡፡
- የማህበረሰቡን ከድንገተኛ አደጋ ማንቂያ መልዕክቶችን በመቅረፅ ግንዛቤ ያሰርፃል፡፡
- ዘርፈ ብዙ ምላሽ በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ የሚመለከታቸውን ተቋማት በሚላሽ አሰጣጡ ላይ እንዲሳተፍ ያደርጋል፡፡
- አስፈላጊ የህክምና ግብዓትና ቁሳቁሶችን ያሟላል፡፡
- ተለላፊ ያልሆኑ ሽታዎችን አስመልክቶ በተጋላጭነትና መንስኤ ላይ ከአኗኗር ዘይቤ፣ ጤናማ ካልሆኑ ልማዶች ላይ ንቃተ ጤና ያሰርፃል፡፡
- ድህረ ወረርሽኝና የድንገተኛ አደጋ ተጎጅዎችን መልሶ ማቋቋም ተግባራትን ያከናውናል፡፡