የግዥ ስራ አስፈጻሚ የሚኒስትሪውን የግዥ ዕቅድ በማዘጋጀት እንደ አስፈላጊነቱ በማሻሻል ወደ ተግባር መግባትና ከዚህ በታች የተመለከቱትን የግዥ መርህዎችን ማሳካት ነው
- በግዥ አፈጻጸም ረገድ ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችለውን ጥቅም ማስገኘት
- አድልዎ አለማድረግ
- ግልጸኝነት
- ተጠያቂነትና ግብረ ገብ
ራዕይ
የተሻለ የግዥ እና የውል አስተዳደር ሥርዓትና አፈጻጸም እንዲኖር የሚያደርግ የግዥ ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ መገኘት
ተልዕኮ
ዘመናዊ የግዥ እና የውል አስተዳደር ስርዓትን በመከተል የመፈጸምና የማስፈጸም አቅምን በዘላቂነት በመገንባት ቁጥጥርና ክትትልን በማጠናከር የመንግስት ግዥና የውል አስተዳደር ፍትሃዊ፣ ቀልጣፋ፣ውጤታማ እንዲሁም ግልጸኝነትና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ
የግዥ ስራ አስፈጻሚ ተግባርና ኃላፊነት
- የግዥ ፍላጎት መለየት
- የግዥ ፍላጎት ከሚኒስትር ጽ/ቤቶች እና ከሥራ አስፈጻሚ ክፍሎች ማሰባሰብ
- አመታዊ የግዥ እቅድ ማዘጋጀት
- ከሠነድ ዝግጅት እስከ የውል ስምምነት ስራዎች መከታተልና አስተዳደር መፈጸም
- የግዥ ስራ አስፈጻሚ የሚኒስትሪ መስሪያቤቱን የግዥ ስራ ያስተዳድራል ጥራቶችን ይከታተላል፣የግዥው ሂደት የታለመና በተቀላጠፈ የጊዜ ገደብ መጠናቀቁን ይቆጣጠራል.