የንብረት አስተዳደር፣ የትራንስፖርት ስምሪትና ተሽከርካሪ ጥገና ፣ የግቢ ደህንነትና ጥበቃ፣ የጽዳት አገልግሎት፣ የግቢ ውበት፣ቤቶች አስተዳደርና የሁለገብ ጥገና፣ ኘሮቶኮል የስብሰባና ስልጠና እና የልዩ ልዩ አገልግሎቶች ሥራዎችን ያቅዳል፣ ያደራጃል፣አፈፃፀሙን ይገመግማል፣ ማሻሻያ ያደርጋል፡፡
ስትራቴጅክ ዓላማዎች
- ዘመናዊ የንብረት አያያዝን ተግባራዊ በማድረግ በተቋሙ ያለውን የንብረት አስተዳደር ከማዘመን አንጻር የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን ጎን ለጎንም ከአገልግሎት ውጪ የሆነ ንብረቶችንም እሴት በሚጨምር መልኩ እንዲወገዱ ማድረግ፡፡
- በዳይሬክቶሬቱ ያለውን የጤና ማሻሽያ ልማት ሰራዊት አደረጃጀት በኬዝ ቲም፣ በትራንስፎርሜሽንና በዳይሬክቶሬት ፎረም የተደራጀ ሲሆን ይህን አደረጃጀት በመጠቀም ውጤት ላይ መሰረት ያደረገ እንቅስቃሴን በመተግበር በዳይሬክቶሬቱ የሚሰጠውን አገልግሎት ማሻሻል፡፡
- በስራ አስፈፃሚው ያለውን የክህሎት ውስንነት ለመቅረፍ በተቋሙ ካሉ ሌሎች የስራ ክፍሎች ጋር በመተባበር በአስፈፃሚው ስራ ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ለውጥን መፍጠር እና ችግሩን ለመቅረፍ የሚያስችሉ የክፍሎት፣ የአመለካከት እና የእውቀት ስልጠናዎችን በመስጠት የተሻለ ደረጃ ላይ ማድረስ፡፡
በአስፈፃሚው ስራ የሚገኙ የስራ ቡድኖች
- የንብረት ስራ አመራር አገልግሎት ቡድን
- የትራንስፖርትና ነዳጅ አስተዳደር ቡድን
- የተሽከርካሪ ጥገና ቡድን
- የህንጻና ቤቶች አስተዳደር ቡድን
- የስልጠና ስብሰባ እና ኘሮቶኮል ቡድን
- የጋራ አገልግሎት ቡድን
የንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ቁልፍ የትኩረት መስኮች/Flagship initiative/
- ጽዱ እና ለስራ ምቹ የስራ አካባቢን ለመፍጠር የጽዳት አገልግሎት አሰጣጡ በስታንዳርድ የተጠበቀ እንዲሆን በተዘጋጀው ቼክ ሊስት መሰረት ተግባራዊ ስለመደረጉ ማረጋገጥ፣
- በቴክኖሎጂ የታገዘ የንብረት ምዝገባ፣አወጋገድ እና የቁጥጥር ስርዓትን በመዘርጋት የተቋሙን የንብረት ብክነትን በ25%መቀነስ
- የጂፒኤስ ገጠማ በማከናወን እና የፊሊት ማናጅመንት ስርዓትን መቶ በመቶ በመተግበር የነዳጅ አጠቃቀምን በ25% መቀነስ
- የሴኩሪቱ ካሜራ በማስገጠም እና የእሳት አደጋ መከላከያ መሳሪያዎችን በማስገጠም የህንጻና ምድረ ግቢ ደህንነትን በ100% ማረጋገጥ፤
የሥራ ክፍሉ ዋና ዋና ተግባራት፤
- የሥራ ክፍሉን በጀት ያቅዳል፣ ለታቀደለት ዓላማ መዋሉን መከታተል፣ መቆጣጠር እና የሥራ ክፍሉ በሰው ኃይል፣ በጀት እና በግብዓት እንዲሟላ ማድረግ፡፡
- በሥራ ክፍሉ የሚገኙ ሰራተኞች በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት እንዲሰጡ የሥራ አፈፃፀም ምዘና በማካሄድ የአቅም ክፍተት ያለባቸውን ባለሙያዎች አቅማቸው የሚያሳድጉበትን መንገድ/ዘዴ ይቀይሳል፣
- ለቢሮ ሥራ እና ለሥልጠና የሚያገለግሉ የማቴሪያል ፍላጎቶች እና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶችን ጭምር እንዲሟላ ማድረግ፣
- በበጀት ዓመቱ ለክፍሉ የሚያስፈልጉትን የጽዳት ዕቃዎች በጀት ይይዛል፣ የደንብ ልብስ፣ ግዥ እንዲፈፀም ክትትል ያደርጋል፣አፈፃፀሙን ይከታተላል በአግባቡ ስራ ላይ መዋላቸውን መቆጣጠር፣
- በተቋሙ የውሃ ፣ የመብራት ፣ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት መስራታቸውን በማረጋገጥ የአገልግሎት ክፍያዎች ወቅቱን ጠብቆ አገልግሎቱን ለሰጡት መስሪያ ቤቶች መከፈላቸውን እና ሲበላሹ በአስቸኳይ መጠገናቸውን ማረጋገጥ፣
- ገቢ የሚደረጉ ቋሚም ሆነ አላቂ ዕቃዎችን በስቶክ ከፍተኛ ክምችት እንዳይኖር ተገዝተው የሚገቡትንም መመሪያውን ተከትሎ ለተጠቃሚ በወቅቱ አገልግሎት ላይ መዋሉን መቆጣጠር፣
- የሚወገዱ ንብረቶችን ለማስወገድ የዕቃዎችን ዝርዝር ዝግጅትን ያስተባብራል፣ መመሪያውን ተከትሎ መወገዳቸውን ክትትል ያደርጋል፣ አፈፃፀሙን ሪፖርት ማቅረብ፣
- የሚወገዱ ንብረቶች በመመሪያና ደንብ መሰረት መሆኑን ያረጋግጣል፣ በስጦታ የሚሰጡትን ለመ/ቤቱ የበላይ ኃላፊ በማፀደቅ ስጦታ ለተፈቀደላቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርቶች በየመስሪያ ቤቶቹ የገቢ ሰነዶች ገቢ ማድረጋቸውን ያረጋግጣል ፣ መቆጣጠር፣
- ዓመታዊ የንብረት ቆጠራ ተግባራት ይመራል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡፡ ዓመታዊ የንብረት ቆጠራ መሠረት አድርጎ የሚጠገኑትን ማስጠገን እና የሚወገዱትን በመመሪያና በደንቡ መሠረት እንዲከናወን ማድረግ እና ቆጠራውን መሠረት አድርጎ የሚጠገኑትን ማስጠገን አና የሚወገዱትን በመመሪያና በደንቡ መሠረት በፍጥነት እንዲወገዱ በማድረግ የአወጋገድ ማጠቃለያ ሪፖርት መዘጋጀቱን መቆጣጠር፣
- በመንግስት ተሽከርካሪዎች አጠቃቀም ደንብና መመሪያ መሠረት ለተሽከርካሪዎች የነዳጅ የኢንሹራንስና የተለየየ መኪና መለዋወጫ እቃዎች ግዥ የሚሆን በጀት እንዲያዝ ያደርጋል፣ የተሽከርካሪዎች ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ እንዲደረግላቸው ያደርጋል፣ አስፈላጊው ሂደት ያላላፉትን ተገቢው ጥገና ተደርጎላቸው ለምርመራ ብቁ እንዲሆኑ ማድረግ፣
- ቴክኖሎጂን በመጠቀም በተሽከርካሪ ስምሪት ቁጥጥር ሶፍትዌር በመታገዝ በመ/ቤቱ የሚገኙ ተሽርካሪዎችን ከየስራ ክፎሎች የሚቀርቡ ጥያቄዎች መሰረት የሥምሪት ሥራዎች መከናወናቸውን ይቆጣጠራል የነዳጅና ቅባት ዕደላዎችና አጠቃቀም በመመሪያው መሰረት መፈጸማቸውን ማረጋገጥ፣
- ለተሽከርካሪዎች የትራንስፖርት ህግና ደንብ በሚይዘው መሰረት የቅድመ ብልሽት የቴክኒክ ምርመራ በወቅቱ ማድረግ እና ለሚደርሱ ድንገተኛ የተሽከርካሪ አደጋዎች በኢንሹራንስ ህግ መሰረት ተፈፃሚ እንዲሆኑ ክትትል ማድረግ፣
- ለተለያዩ የሥራ ክፍሎች በጋራና በተናጠል የየዕለት ሥራቸውን የሚያከናውኑበት በቂ ተሽከርካሪ መመደቡንና አገልግሎቱ በተሟላ መልኩ መሰጠቱን ማረጋገጥ፣
- ለመስክ ሥራ የሚመደቡ ተሽከርካሪዎች ለሥራ ከመሠማራታቸው በፊት ተገቢው የቴክኒክ ምርመራና ጥገና መደረጉን እና የተሟላ የመድን ሽፋን የተገባላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣
- ለመስክ ሥራ የሚመደቡ ተሽከርካሪዎች ለሥራ ከመሰማራታቸው በፊት ተገቢው የቴክኒክ ምርመራና ጥገና መደረጉን እና የተሟላ የመድን ሽፋን የተገባላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣
- ለተሽከርካሪዎች የሚያስፈልጉ የነዳጅ፣ የቅባትና ሌሎች የመወዋወጫ እቃዎች መሟላታቸውንና ለተገቢው አገልግለት መዋላቸውን ማረጋገጥ፡፡
- ለጥገና ጋራዥ የገቡ ተሽከርካሪዎች በአስቸኳይ ተጠግነው ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ማስቻል፣
- ጥገና ለሚያስፈልጋቸው የተቋሙ ቋሚ ንብረቶች ቅድመ ጥናት በማድረግ ጥገና የሚያስፈልጋቸው የቢሮ መገልገያ ወንበሮች ፣ ጠረጴዛዎች፣ የፎቶ ኮፒ ማሽኖች፣ የውሃና ኤሌትሪክ ብልሽቶች በጥናቱ መሠረት እና በቀረቡ የጥገና ጥያቄ መሰረት አስፈላጊው ጥገና መደረጉን መከታተል፣
- በተቋሙ ውስጥ የእሳት አደጋ መከላከያዎች በተገቢው ቦታ መተከላቸውንና በየወቅቱ እየተፈተሹ ለአገልግሎት ብቁ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣
- ጥገና ለተከናወነባቸው የክፍያ ጥያቄዎች ሲቀርቡ አጣርቶ ተገቢው ክፍያ እንዲፈጸም ለፋይናንስና የሥራ ክፍል እንዲደርስ ማድረግ፣
- የስልክ፣ መብራትና ውሃ አገልግሎቶች በትክክል እየተሰጡ መሆኑንና ብልሽት ሲያጋጥም አስፈላጊው ጥገና ማድረግ እና የአገልግሎቶች ወርሃዊ ክፍያ በወቅቱ እንዲፈጸም ማድረግ፣
- ቢሮዎች ፣መፀዳጃ ቤቶች ፣ የግቢው ጽዳት ሥራ በአግባቡ መፈፀሙንና ለሥራ ምቹ መሆኑን ማረጋገጥ፣
- የተቋሙ ቅጥር ግቢዎች ያማሩና ማራኪ ለማድረግ በአበባና በተክሎች መዋባቸውን ማረጋገጥ፣
- የጽዳትና ውበት ሠራተኞች የሥራ ስምሪት አፈጻጸምን ይከታተላል፣ይገመግማል፡፡
- ቴክኖሎጂን በመጠቀም በሲሰቲቪ ካሜራ በመታገዝ ተቋሙ የተጠናከረና አስተማማኝ የ24 ሰዓት የጥበቃ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ማረጋገጥ፣
- ከተገልጋዮች የስብሰባ ስልጠናና የጤና ሁነት ዝግጅት የማስተባበር አገልግሎት ጥያቄ ከኘሮፖዛል ጋር መቀበል አና የሚያስትናብሩ ባለሙያዎች /አሸሮች/ መመደብ፣ ሲጠናቀቅ የክፍያ ሰነዶችን አረጋግጦ ከሆቴል በመረከብ የክፍያ መጠየቂያ አዘጋጅቶ ለፋይናንስ በማስተላለፍ ክፍያው መፈጸሙን መከታተል፣
- የኘሮቶኮል አቀባበል የሚያስፈልጋቸው የኘሮቶኮል አቀባበል የተደረገላቸውን ተሳታፊዎች በኘሮቶኮል መርህ መሠረት እንግዶች ለስብሰባ ወደ አዳራሾች ሲመጡ በመቀበልና ወደ ቦታቸው መውሰድና የቅርብ ክትትል ማድረግ፣
- የተገልጋይ እርካታ ዳሰሳ ጥናት በማካሄድ፣ ከውስጥና ከውጪ ደንበኞችና አጋር አካላት አስትያየት በመሰብሰብ ከደንብና መመሪያ ጋር በማስተሳሰር የደንበኞችን እርካታ ተደራሽ ማድረግ፣
- የሥራ ክፍሉን የሥራ እንቅስቃሴ የሚገለፅ በየወሩ ፣ በየሩብ ዓመቱ በየግማሽ ዓመት እና ዓመታዊ ሪፖርት ያዘጋጃል ለበላይ ኃላፊም ማሳወቅ፣
- ምርጥ ተሞክሮ በመቀመር ከተቋሙ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ተግባራዊ ማድረግ እና ማሻሻል፣
- አዳዲስ የአሰራር ስራ ስርዓቶችን ይዘረጋል፣ ተግባራዊነታቸው ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣