የአስፈፃሚ ኃላፊነት ፡-
የአስፈፃሚው የሥራ አላማዎች ፡-
- የሥራ ክፍሉን ሥራዎች በማቀድ፣ በማደራጀት እና በመምራት፣ የስነምግባር እና ግንባታ ሥልጠና በመስጠት ሰራተኞች ሙስናን በመጠየፍ በስነምግባር ታንፀው እና ሙያዊ የሥራ ዲስፒሊን አክብረዉ በኃላፊነት ስሜት ህዝብን የማገልገል ግዴታቸዉን እንዲወጡ ማድረግ፣
- የሥራ ክፍሉን ሥራዎች ከሙስና እና ብልሹ አሠራር የፀዱ እንዲሆኑ በክትትልና ድጋፍ አሰጣጥ መሰረት ድጋፋዊ የመስክ ምልከታ በማድረግ ተገቢዉን ምክረ ሀሳብ እና ግብረ መልስ በመስጠት መደገፍ፣
- ለሙስና እና ለብልሹ አሠራር የተጋላጭነት ሥጋት ያለባቸዉን የተለዩ የሥራ ዘርፎች በመለየት የዳሰሳ ጥናት ማካሄድ፣ መረጃዉን መተንተን እና ደረጃ በመስጠት ሙስና እና ብልሹ አሠራር መከላከል የሚያስችል አሠራር መዘርጋትና ተግባራዊነቱን መከታተልና መደገፍ፣
- በተቋሙ ዉስጥ የሚገኙ ክቡራን አመራሮች እና ሠራተኞችን የኦንላይን የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ሥርዓትን በማስተባበርና በመምራት ሙስና እና ብልሹ አሠራርን መከላከል፣
- ለሙስና እና ብልሹ አሠራር ጥቆማ አቀራረብ እና አቀባበል ምቹ ሁኔታዎችን በማመቻቸት የሚቀርቡ ጥቆማዎችን በማጣራት የአርምት እርምጃዎች እንዲወሰዱ ከማስደረግ ጎን ለጎን ጠቋሚዎች እንደአስፈላጊነቱ ህጋዊ ከለላ እንዲያገኙ ማድረግ፣
- በተቋሙ ውስጥ ስነ-ምግባር ማክበር እና ሙስናን በመከላከል የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ተልዕኮን ተግባራዊ ማድረግ ነዉ።
ራዕይ፡-
- ጤናማ፣ አምራች እና የበለፀጉ ኢትዮጵያውያንን ማየት። (ይህ የጤና ሚ/ር ራዕይም ነዉ።)
- በ2030 ኢትዮጵያን በአፍሪካ ዉስጥ የብልጽግና ተምሳሌት /አርአያ/ ሆና ማየት (ይህ የስነ ምግባር እና የፀረ–ሙስና ኮሚሽን ራዕይ ነዉ።) የሥራ ክፍሉም ይህንኑ ራዕይ ለማሳካት ይሠራል፡፡
ተልዕኮ፡-
- አጠቃላይ የጤና አገልግሎት ፓኬጅ በማቅረብ እና በመቆጣጠር ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የህብረተሰቡን ጤና እና ደህንነት መጠበቅ። (የጤና ሚ/ር - ኢትዮጵያ ተልዕኮ)
- ሙስናን መከላከል የሚያስችል አመለካከት እና ግንዛቤ በማሳደግ ጠንካራና ኃላፊነቱን የሚወጣ ተቋማዊ አደረጃጀት መፍጠር (ይህ የፌዴራል የስነምግባር እና የፀረ–ሙስና ኮሚሽን ተልዕኮ ነዉ።) የሥራ ክፍሉም ይኸው ተልዕኮ እንዲሳካ ይሠራል፡፡
የአስፈፃሚ ሚና እና ኃላፊነቶች፡-
በሥራ መደቡ ዝርዝር መግለጫ (Job description) ላይ እንደተገለጹት፣ የሥራ ኃላፊነቶች እና የሚጠበቁ ውጤቶች የሚከተሉት ናቸው።
- የሥራ ክፍሉን ሥራ ማቀድ፣ መምራት እና ማስተባበር ፣
- የስነምግባር ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት ሙስናን የመከላከል ሥራ ውጤታማነት ማረጋገጥ፣
- የሙስና ተጋላጭነት ስጋት አካባቢዎችን ለይቶ ጥናት በማካሄድ፣ ደረጃ መስጠት እና የመከላከያ ስልቶችና የአሠራር ምክረ–ሐሳቦችን መስጠት እና አፈጻጸሙን ማረጋገጥ፣
- የኦንላይን የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ በማስተባበር እና በአሠራር ላይ የጥቅም ግጭቶች የሚያስከትሉ አፈፃፀሞችን መከላከል ፣
- የመረጃ (ጥቆማ) አቀራረብ ስልቶችን በማመቻቸትና በማስተዋወቅ መረጃዎችን በማመንጨት፣ ከጠቋሚዎች መረጃን በመቀበል እና በማጣራት የሚከሰቱ ሙስና እና ብልሹ አሠራሮች በፀረ ሙስና ህጎች ደንቦችና መመሪያዎች መሰረት ቀርበዉ እንዲታረሙ ማድረግና አፈጻጸሙን መከታተል፣