ስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ

የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ /ቤት የተቋቋመው በጤናው ሴክተር ውስጥ ያሉትን የአንድ እቅድ፣ አንድ በጀት እና አንድ ሪፖርት መርሆዎችን እውን ለማድረግ እንዲሁም ዘላቂ የጤና ፋይናንስ አቅርቦትን እና በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ በመስጠት የሀብት አጠቃቀምን ለማረጋገጥ ነው።

የስራ አስፈጻሚ /ቤት  በአራት ቡድኖች የተዋቀረ ነዉ፡-

  • የጤና መረጃና ስታስቲክስ ቡድን፤
  • እቅድ፣ በጀት፣የክትትል እና ግምገማ ቡድን፤
  • የተራድኦ እና የፕሮጀክት አስተዳደር ቡድን እና
  • የጤና ኢኮኖሚክስ፣ፋይናንሲንግ ቡድን ናቸው።

የስራ አስፈጸሚ /ቤት ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸዉ

    • በጤናው ዘርፍ የጤና ስርዓት አፈጻጸምን ለማሻሻል እና የጤና ውጤቶችን ለማሻሻል በማስረጃ ላይ የተመሰረተ እቅድ፣ ክትትል እና የውሳኔ አሰጣጥ ባህልን ማሳደግ።
    • የገንዘብ ክፍተቶችን መለየት፣ ያሉትን ሃብቶች ማፕ ማድረግ እና ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የጤና ስርዓት ኢንቨስትመንቶች ሀብቶችን ማሰባሰብ;
    • ያሉትን ሀብቶች ቀልጣፋ አጠቃቀምን እና ፍትሃዊ ምደባን ማረጋገጥ እና ለጤና አገልግሎት የፋይናንስ ስጋት ከለላ ለማጠናከር የሚደረጉ ጥረቶችን መምራትና ማስተባበር።
    • በጤናው ሴክተር የሚገኙ ባለድርሻ አካላትን ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከርና የግንኙነት ስርዓቱን የማስተባበር።
    • በጤና ላይ የጋራ ራዕይን እና አጀንዳን በማጎልበት የግል ለትርፍ እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ባለድርሻ አካላት ተሳትፎን ማሳደግ፤  የሚያስችሉሁኔታዎችን ማመቻቸት።

ራዕይ 

በማስረጃ ላይ የተመሰረተ ዕቅድ፣ በጀት እና የውሳኔ አሰጣጥ ስርዓትን በማስፈን ጤናማ፣ ምርታማ እና የበለጸገ

ማህበረሰብ ተፈጥሮ ማየት።

ተልዕኮ፡

የስራ ክፍሉ ተልዕኮ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎትን ለሁሉም ለማዳረስ የሚያስች ልየ ጤና ስርዓት አፈጻጸምን በቀጣይነት ለማሻሻል በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ የመስጠት ባህልን ማሳደግ ነው። ለዚህም ስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ አንድ ዕቅድ አንድ በጀት እና አንድ ሪፖርት መርሆችን በየደረጃው ተቋማዊ ያደርጋል የዘርፉን ስትራቴጂካዊ እና ዓመታዊ ዕቅዶች አሳታፊ በሆነ ሂደት ያዘጋጃል ፤ጠንካራ የጤና መረጃ ስርዓት ይተገብራል እንዲሁም መረጃን ለውሳኔ የመጠቀም ባህልን ያጎለብታል ፣የፋይናንስ ክፍተቶችን ይለያል ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የጤና ፕሮግራሞች እና ለአደጋ ጊዜ ምላሽ መስጠት የሚያስችል ሃብት ያሰባስባል፣ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል እና ውጤታማ የሃብት አጠቃቀምን ለማረጋገጥ በጤና ኢኮኖሚክስ እና ፋይናንስ ላይ መረጃዎችን ያጠናቅራል፣ይተነትናል እንዲሁም የጤናው ዘርፍ ባለ ድርሻ አካላትን ቅንጅት ያስተባብራል። በተጨማሪም የግሉ ዘርፍ ተሳትፎን ውጤታማነት ያረጋግጣል።

ተግባርና ኃላፊነቶች-

ስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ የዘርፉን ዕቅድና በጀት የማውጣት፣ሃብት የማሰባሰብ፣ ክትትል፣ ግምገማና ቅንጅታዊ አሰራራርን የማጠናከር ተግባራትን የመምራት ትልቅ ኃላፊነት አለበት

  • የስትራቴጂክ እና ዓመታዊ ዕቅድ ማዘጋጀት፡- ስራ አስፈፃሚ/ቤት የዘርፉን ስትራቴጂዎችንና ዕቅዶችን ከሃገሪቱ የረዥም ጊዜ ስትራቴጂክ ዕቅዶች እና ዓለም አቀፍ ግቦች ጋር በማጣጣም ያዘጋጃል። ስራ አስፈጻሚው በየደረጃው ያለውን የዘርፉ ስትራቴጂክና ዓመታዊ የዕቅድ ዝግጅትን ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ባሳተፈ መልኩ እና አንድ የጤና ዘርፍ ዕቅድ እንዲታቀድ የዕቅድ ዝግጅት ሂደቱን በበላይነት ይመራል፡፡
  • ጠንካራ የጤና መረጃ ስርዓት መተግበር: የሥራ አስፈፃሚው ጽሕፈት ቤት በየደረጃው ጥራት ያለው መረጃ ለማግኘት እና ተደራሽነቱን ለማረጋገጥ የጤና መረጃ ሥርዓቶችን ማዘጋጀት ፣ መሞከር እና የመተግበር ስራ ስፈጸማል፡፡በተጨማሪም የመረጃ ጥራትን በቀጣይነት ለማሻሻል እና የጤና ስርዓትን አፈፃፀም ለማሻሻል እና የጤና አገልግሎቶችን ጥራት እና ፍትሃዊነት ለማሻሻል በማስረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ የመስጠት ባህልን ለማዳበር ይሰራል፡፡ ሥራ አስፈፃሚው ቅድሚያ የሚሰጠውን የጤና መረጃ ንዑስ-ስርዓቶችን ለዲጂታይዜሽን ይለያል ፣ የሶፍትዌ ርልማት መስፈርቶችን ያዘጋጃል እንዲሁም የበለጸጉ ሶፍትዌሮችን በተዘጋጀው መስፍርት መሰረት መሆኑን ይፈትሻል። በሁሉም የጤና ስርዓት ደረጃዎች የጤና መረጃ ንዑስ ስርዓቶችን ተግባራዊ ማድረግ እና ቅንጅቶችን ለማረጋገጥ የጤና መረጃ ስርዓት አስተዳደርን እንዲጠናከር ያደርጋል፡፡
  • ክትትል፡ የጤና ስርዓት አፈፃፀም ቀጣይነት ያለው መሻሻል እንዲኖር የአፈፃፀም ክትትልን ማረጋገጥ ከአስፈፃሚው ዋና ዋና ተግባራት አንዱ ነው። ይህ በዓመታዊ እና ስትራቴጂክ ዕቅዶች ውስጥ ከዒላማዎች አንጻር ያለውን ሂደት ለመከታተል የተለያዩ ዘዴዎችን መተግበር እና መድረኮችን መዘርጋት ይጠይቃል።ክትትል የአፈጻጸም ግምገማዎችን፣የቁጥጥር ጉብኝቶችን የመደበኛ መረጃ ትንተናን የመረጃ ውጤቶችን ማመንጨት፣መጠቀም እና ማሰራጨት የዘርፉ ተዋናዮችን በመረጃ ማዳረስን ያካትታል።
  • ግምገማ፡ ይህ ተግባር የስራ አስፈፃሚው ከሌሎች የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ ኤጀንሲዎች እና የልማት አጋሮች ጋር በመቀናጀት ከሚጫወታቸው ቁልፍሚናዎች አንዱ ነው። የጤና ሴክተር ስትራቴጂክ እቅድ ውጤቶችን ለመለካት የስራ አስፈፃሚ ቢሮ የተለያዩ ግምገማዎችን ይመራል። የሥራ አስፈፃሚው የጋራ ግምገማ ተልዕኮ፣ መካከለኛ ዘመን እና የስትራቴጂክ ዕቅዶች የማጠናቀቂያ ግምገማ እንዲሁም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ፕሮጀክቶችን ጨምሮ ዋና ዋና ግምገማዎችን ያስተባብራል። በተጨማሪም ስራ አስፈጻሚው ከሚመለከታቸውአካላት ጋር በመተባበር የትግበራ ምርምሮችን አገር አቀፍ ደረጃ የዳሰሳ ጥናቶችን፣ የክትትል ሌሎች የምርምር ሥራዎች እንዲከናወኑ ድጋፍ ያደርጋል
  • ላዘላቂ የሃብት ማፈላለግ ስራዎችን ማከናወን የስራ አስፈጻሚ /በት ኦፊሱ በጤናዉ ዘርፍ ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ የልማት አጋር ድርጅቶች በሚያበረክቱት ሙያዊ እገዛና እና የገንዘብ ድጋፍ  እንዲሁም በተሰማሩባቸዉ እና የገንዘብ ድጋፍ በሚያደርጉባቸዉ የጤና አገልግሎት ዘርፎች እና የተመረጡ የጤና ተቋማት፤ በክልሎች፤ በመደበኛ የጤና አግልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም የጤና ድንገተኛ አደጋዎች ልየታ እና ግብረመልስ ምልከታና እና ድጋፍ ተለይተዉ ማፕ የማድረግ ስራ ያከናዉናል፡፡ ለጤናዉ ዘርፍ የሚያስፈልጉ የገንዘብ ግብዓቶችን የተለያዩ የሃብት ማሰባሰቢያ መንገዶችን በመጠቀም  የተለያዩ አማራጭ ዘዴዎችን ተግባራዊ በማድረግ አዳዲስ እና ቃል የተገባባቸዉን የገንዘብ ግብዓቶችን ክትትል በማድረግ ለታቀደለት ኣላመ እንዲዉሉ ያደርጋል፡፡ ለአጋር ድርጅቶች እና ለተለያዩ ገንዘብ የሚገኙበትን በአገር ዉስጥና በዉጭ አገር የሚገኙ ተቋማት አስፈላጊ ሰነዶችን፤ፐሮፖሳሎችን በማዘጋጀት ቃል ለተገባባቸዉ ስርዓት በመዘርጋት የተገኙ ሃብቶችን ወደ ሲስተም እንዲገቡ ያደርጋል፡፡
  • የተራድኦ እና ፕሮጄክት አስተዳደር፡ የስራ አስፈጻሚ ኦፊሱ ከመንግስት በመደበኛነት የሚመደቡ በጀቶችን፣ በብድር እና በእርዳታ ለፕሮጄክት ማሰፈጸሚያ የተገኙ ሃብቶችን፣ በብድር እና በፕሮግራሞች የሚመጡ ሃብቶችን ከገንዘብ ሚኒስቴር እና ከልማት አጋር ድርጅቶች ጋር በመናበብ የገንዘብ ማስተዳደር ስራን በዋናነት ያግዛል፡፡ በሃብት አስተዳደር እና ፕሮጄክት ማናጅመንት ስራዎች ላይ የአቅም ግንባታ ስራዎችን የማከናወንና በተለይም መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት በሚያቀርቡት ፕሮጄክት በስራ ላይ የሚዉሉ ገንዘቦችን በፕሮጄክ መገምገም እና መፈራረም እንዲሁም አፈጻጸማቸዉን በመገምገም ገንዘቡ ለታለመዉ ዓላመ መዋሉን ይከታተላል፡፡ በጤናዉ ዘርፍ የተመደቡ የመንግስት እና የዉጭ እርዳታና ብድር ገንዘብ አጠቃቀም ላይ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ምላሽ ይሰጣል፡፡
  • ዘላቂ የጤና ፋይናንስ ስርአት እንዲኖር ማስቻል፡- የስራ አስፈፃሚ /ቤት በመረጃ ላይ የተመሰረተ የሀብት ድልድል፣ ስርጭት እና አጠቃቀም አንዲኖር ለማስቻል የተለያዩ የኢኮኖሚያዊ እና ፋይናንስ ትንታኔዎችን ስራት ተግባራዊ ያደርጋል። የፅ/ቤቱ  የብሄራዊ የጤና ወጪ ጥናቶችን፣ የመንግስት ጤና ወጪ ግምገማዎችን፣ ስትራቴጂክ የወጪ ትመና፣ ፊሲካል ስፔስ እና የውጤታማነት ትንተና እኒዲሁምኢኮኖሚያዊ ግምገማዎችን ይሰራል። በተጨማሪም ቢሮው የጤና ክብካቤ ፋይናንስ ስትራቴጂ፣ ውጤትን መሰረት ያደረገ የፋናንስ ስርአት እና የመጀመሪያ ትውልድ የጤና ፋይናንስ ማሻሻያ ሪፎርሞችን (የአስተዳደር ቦርድ፣ የተጠቃሚ ክፍያ አወሳሰን፣ የገቢ አሰባሰብና አጠቃቀም፣ ያለክፍያ የሚሰጡ የጤና አገልግሎቶች፣ የነፃ ህክምና፣ የአማራጭ/የግል ህክምና በመንግስት ተቋም ማቋቋም እና ክሊኒካል ያልሆኑ አገልግሎቶችን ለሶስተኛ ወገን መስጠት) በተመለከተ ክለሳ እና ትግበራን ይመራል። በተጨማሪም የማህበራዊ እና የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ስርዓቶችን ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፡፡ የተለያዩ የገንዘብ ማግኛ ምንጮችን በማፈላለግ ለጤና ሴክተር ተጨማሪ ሃብት ያፈላልጋል፡፡
  • የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ማሳደግ፡- የግሉ ሴክተር በጤና ሥርዓቱ ውስጥ ውጤታማ ተሳትፎ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ለህብረተሰቡ ለማዳረስ ትኩረት የሚሰጠዉ ጉዳይ ነዉ፡፡ በዚህም መሰረት የስራ ክፍሉ  በግሉ ዘርፍ ተሳትፎ የሚየመጣውን ካፒታልን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ይሰራል የግሉ ሴክተር ተሳትፎ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ተደራሽነት እና አቅርቦትን ለማረጋገጥ እንዲሁም በመንግስት እና በግሉ ሴክተሮች መካከል ውጤታማ ቅንጅት በመፍጠር የውጤታማነት ማሻሻያ በማድረግ ላይ ያለመ  ስራ ያከናዉናል፡፡ በተጨማሪም  በጤናው ዘርፍ MOF-PPP ደይሬክቶሬት ጀነራል አስተባባሪነት PPP ፕሮጄክቶችን ያዘጋጃል፣ ይተገበራል፣ ይገመግማል።
  • የተናበበ  እና  የተጣጣመ እቅድ እና በጀት ስርዓት: ስራ አስፈፃሚ /ቤት ከሚያከናዉናቸዉ ስራዎች  ዋናዉ በፓሪስ አለም አቀፍ ጉባኤ የተላለፈዉን የእርዳታ ፍትሃዊነት እና አግባባዊ አጠቃቀምን ዉሳኔ መሰረት አገራችን የተቀበለችዉን የአንድ ዕቅድ የአንድ በጀት እና አንድ አፈጻጸም ሪፖርት መርህን ተግባራዊ የማድረግ ዋነኛዉ ነዉ፡፡ የተለያዩ የልማት አጋር ድርጅቶችን እና መንግስታዊ ተቋማትን እንዲሁም የግሉን ዘርፍ ያሳተፈ የዕቅድ፣ የበጀት፣የትግበራ እና የክትትል ስራዎች አሳታፊ በሆነ መልኩ ያከናዉናል፡፡ ከጤናዉ ሴክተር ስትራቴጂክ እቅድ ጋር በተናበበ የጋራ የትብብር እና አሳታፊነት ስርዓት ተግባራዊ በማድረግ ድግግሞሽ እና የሃብት ብክነትን በማስቀረት የተደጋገፈ የስረ ሂደትና ትብብር እንዲኖር ይሰራል፡፡ በመርሁ መሰረት የመንግስትን እቅድ መነሻ ያደረገ የተናበበ እና የተጣጣመ ዕቅድ በጀት እና ሪፖርት እንዲኖር በማድረግ እንዲሰራ የአሰራር መመሪያዎችን ተግባራዊ ያደርጋል፡፡ የተናበበ እና የተደጋገፈ ስራ እንዲተገበር የተዘጋጀዉን ማኑዋል መሰረት በማድረግ የተቀመጡ የሃላፊነት እና የአሳታፊነት ስርዓቶችን እንዲተገበሩ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ፡፡ የቅንጅታዊ አሰራር እና አሳታፊነትን መሰረት አድርገዉ የተቀረጹ አደራጃጀቶችን በተመለከተ አገር አቀፍ የጋራ መድረክ፣ የጋራ የትብብር ኮሚቴ፣ የክልሎች ምክክር መድረክ፣ ከሴክተር መስሪያ ቤቶች በጋራ የሚሰሩ ግብረሃይሎችን፣ ስራዎች ይከታተላል ያስተባብራል፡፡ የስራ አስፈጻሚ /ቤቱ በቋሚነት የጤና ወጪ ሃብት ማግኛ ግብረሃይል በበላይነት የሚመራ ሲሆን የቴና ዘርፉን የሃብት ልየታ በፍላጎት መሰረት የተጣጣመ እንዲሆን አስፈላጊ መመሪያዎችን የማዉጣት፣ የመተግበር እና  የመከታተል ስራዎች  ያከናዉናል፡፡