ራዕይ
- ከፍተኛ ጥራ ያለው የጤና አገልግሎት በማቅረብ የህብረተሰቡ ጤና ተሻሽሎ ማየት
ተልዕኮ
የስፔሻሊቲና ሰብ-ስፔሻሊቲ ህክምና አገልግሎቶች ተደራሽነትና ጥራትን በማሻሻል ለህብረተሰቡ ጥራት የለው የህክምና አገልግሎት ማቅረብ ነው፡፡ ለዚህም የተሻሻለ የድንገተኛና ጽኑ ህሙማን ህክምና፣ አምቡላስ አገልግሎት፣ ተሀድሶና ዲያግኖስቲክ/ምርመራ አገልግሎቶች ትኩረት ተሰቶ ይሰራባቸዋል፡፡ የጤና ባለሙያዎችን የአመራርነት አቅም በማሳደግ እናበቃለን፤ ደህንነቱ ለተጠበቅ የህሙማን ቅብብሎሽ አሰራር ስርዓቶች እንዘረጋለን፤ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ የሆነ የህክምና አገልግሎት በማቅረብ የተሻለ ነገን መፍጠር ነው፡፡
የመሪ ስራ አስፈጻሚ ተግባርና ኃላፊነት
- የስፔሻሊቲና ሰብስፔሻሊቲ አገልግሎቶችን ተደራሽ በማድረግ ዜጎች የጥራቱን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብራና ቅንጅት መስራ
- ሜዲካል ቱሪዝም በሀገራችን ለማበረታታት የሚስችል አደረጃጀት መፍጠር፤ መከታተልና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር መስራት
- የቅድመ ጤና ተቋምና ህሙማን ቅብብሎሽ፣ የድንገተኛና ጽኑ ህሙማን ህክምና፣ የሆስፒታል ማሻሻያና ምርመራ/ዲያግኖስቲክ አገልግሎት፣ የስፔሻሊቲና ተሀድሶ ህክምና አገልግሎት የመረጃ ስርዓት በማጠናከር የሆስፒታሎች አፈጻጸም መከታተል፣ መደገፍ እንዲሁም የጋራ መማማሪያ ጥምረት መፍጠር
- የቅድመ ጤና ተቋም፣ አደጋና የጽኑ ህሙማን ህክምና ተደራሽነት ለማሻሻል እና ህብረተሰቡ በጤና ተቋማት ወደሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ የሚያስችሉ ዕቅዶችን ማዘጋጀት፣ ማስተግበር፣ መደገፍና ሂደቶችን መከታተል
- ለቅድመ-ጤና ተቋምና ህሙማን ቅብብሎሽ፣ ድንገተኛና ጽኑ-ህሙማን ህክምና፣ ሆስፒታልና ዲያግኖስቲክ አገልግሎት ማሻሻያ፣ ስፔሻሊቲና ሰብስፔሻሊቲ እና ተሀድሲ ህክምና አገልግሎቶች የአስተዳደርና አመራር ልማት ስትራቴጂዎችን መቅረጽና መተግበር
- ህሙማንን ደህንነት በተጠበቀና በሚፈለገው ፍጥነት ወደ ጤና ተቋማ ማድረስ እንዲቻል የቅድመ ጤና ተቋም ህክምና አገልግሎትና ትራንስፖርት ስርዓት መዘርጋት
- ጥናትና ምርምሮች ወደ ትግበራ እንዲቀየሩ ምክረ-ሀሳቦችን ማቅረብና ሂደቱን መከታተል
- የሜዲካል አገልግሎት ዘላቂ የፋይናንስ ስርዓት እኒዲኖር ከባለድርሻ አካላት ጋር መስራት፣ አዳዲስ የፋይናንስ ስትራቴጂዎችን ማፈላለግ፣ ውጤታማነታቸውን መመዘን፤ እንዲሁም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የሆስፒታሎችን የውስጥ ገቢ አሰባሰብና አጠቃቀም ለማሻሻል ይሰራል
ሜዲካል አገልግሎት መሪ ስራ አስፈጻሚ አራት ዴስኮች አሉት
- ሆስፒታልና ዲያግኖስቲክ አገልግሎቶች ዴስክ
- ስፔሻሊቲና ተሀድሶ ህክምና ዴስክ
- ድንገተኛና ጽኑ ህሙማን ህክምና አገልግሎት ዴስክ
- የቅድመጤና ተቋምና ህሙማን ቅብብሎሽ አገልግሎት ዴስክ