በጤናው ዘርፍ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የሰጡ የአዲስ አበባ ወጣቶች እውቅና ተሰጣቸው
የጤና ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ወጣቶች በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ጋር በመተባበር በጤናው ዘርፍ የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር በዛሬው እለት አካሂዷል፡፡
እውቅናውን የተሰጣቸው የአዲስ አበባ ወጣቶች ሲሆኑ በቅዱስ አማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ በአለርት ማእከል፣ በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ በጥሩነሽ ቤልጂንግ ሆስፒታል፣ በካቲት 12 ሜዲካል ኮሌጅ፣ በራስ ደስታ ሆስፒታል እና በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒዬም ሜዲካል ኮሌጅ ወስጥ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ ወጣቶች ናቸው፡፡
የእውቅና አሰጣጥ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ እንደ ጤና ሴክትር ብዙ ነገሮችን በገንዘብ እጥረት ምክንያት ማሳካት በማንችልበት አገር ውስጥ የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት መሰረታዊ ጉዳይ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡