Articles

የጡት ካንሰር ግንዛቤ ወር የክብርት ፕሬዚደንት መልዕክት

HE the President

የጥቅምት ወር የጡት ካንሰር ግንዛቤ ወር ነው። የጡት ካንሰር ሴቶችን በከፍተኛ  ደረጃ ያጠቃል። በአገራችን ታካሚዎች ወደ ጤና ተቋም የሚሄዱት ዘግይተው ነው። የሚታዩ ምልክቶችን በጊዜ ለመለየት ቅድመ ምርመራ እንዲደረግ የሚመለከታቸው ሁሉ በቂ ግንዛቤ ሊይዙ ይገባል። ይህ ባለመሆኑ ብዙዎችን አጥተናል።


ከአገራችን የተለያዩ ክፍሎች ለጨረርና ለኪሞ ሕክምና የሚመጡ ሴት ወገኖቻችን መጠለያ ቦታ ስለሌላቸው ለተጨማሪ ችግር ይጋለጣሉ። ችግሩን ለመቅረፍ ለእነዚህ ሕሙማን ማረፍያ ቦታ በማዘገጀት፣  ወደ ሆስፒታል በማመላለስ፣ መድሃኒት ግዢ ላይ በመደገፍ ወዘተ . . . ከሚሠሩ ድርጅቶች መካከል "ፒንክ ሃውዝ" የተባለውን በቅርብ ጎብኝቻለሁ። ይህንንና ተመሳሳይ ተቋሟችን በመደገፍ ሴቶች በጊዜ ከተደረሰበት ሊታከም በሚችል በሽታ እንዳይጎዱ እናድርግ።

"የጤና መድህን አባላትን ቁጥር በማሳደግ የዜጎችን ተጠቃሚነት የማረጋገጡ ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል" የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሠ

lia

አገር አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2014 ዓ.ም ዕቅድ ግምገማ ጉባኤ ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው የስራ አቅጣጫ የሰጡት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሠ እንደተናገሩት የጤና መድህን አባላትን ቁጥር በማሳደግ የዜጎችን ተጠቃሚነት የማረጋገጡ ስራ በ2014 በጀት ዓመትም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡


የጤና መድህን አባላትን ቁጥር በማሳደግና ዘላቂነት ያለው የፋይናንስ ስርዓትን በመፍጠር በጤና ተቋማት ላይ የሚነሱ ችግሮችን ለመቅረፍ እንደሚረዳ የገለጹት ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሠ ይህንን ለማሳካትም ከላይ እስከታች ያለው የጤና መዋቅር አመራር በመደጋገፍና በቅንጅት መንፈስ ሊሰራ ይገባልም ብለዋል፡፡

ፖሊዮን ጨርሶ ለማጥፋት የሚያስችል የክትባት ዘመቻ  በይፋ ተጀመረ

Dr. Dereje Duguma

ከፖሊዮ ነጻ የሆነ አለም እንፍጠር በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ በሲዳማ ክልል በአዋሳ ከተማ እና በደቡብ ክልል ጌዲዮ ዞን ዲላ ከተማ የክትባት ዘመቻ መርሀግብር ያስጀመሩት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ  በመርሀግብሩ እንደተናገሩት የጤና ሚኒስቴር ፖሊዮን ለማጥፋት በመደበኛ ክትባትና በዘመቻ በሚሰጥ ክትባት ከሀገራችን  ለማጥፋት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው።


ባለፉት አመታትም በተከናወነው ስራ ፖሊዮን ማጥፋት ተችሎ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት  በተለያዩ አከባቢዎች  እየታየ ያለውን የልጅነት ልምሻ በሽታ ለማጥፋትም እስከ ጤና ኬላ በተዘረጋ መዋቅር እና ከአጋር አካላት ጋር በተቀናጀ አሰራር እየተተገበረ መሆኑን ተናግረው  ይህም መንግስት ለሕጻናት ጤና መሻሻል ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ማሳያ መሆኑን አስረድተዋል፡፡