በጂግጂጋ ዩኒሸርሲቲ ሼህ ሀሰን የቦሬ ሪፈራል ሆሰፒታል የሚገኘው የኩላሊት እጥበት ማእከል እና የጂግጂጋ የደምና ቲሹ ባንክ በዛሬው እለት በጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ተጎብኝቷል
የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ አመራሮች ከክልሉ የጤና ቢሮ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በሆስፒታሉ የሚገኙ የMRI ክፍልን፣ የኩላሊት እጥበት ህክምና ማእከልን፣ የደምና ቲሹ ባንክን የጎበኙ ሲሆን በተለይ የከተማዋ ህብረተሰብና ባለሀብቶችን በማሳተፍ የተቋቋመው የኩላሊት እጥበት ህክምና ማእከል አገልግሎት አሰጣጥ ተዘዋዉረው ተመልክተዋል።
የኩላሊት እጥበት ህክምና ማእከሉ ከሱማሌ ና ከአካባቢው ለሚመጡ ተካሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ አገልግሎት ተደራሸ እያደረገ እንደሆነ በጉብኝቱ ተገልጿል። በዚህም በ2013 ዓ.ም ለ724 ታካሚዎች አገልግሎቱን መስጠት እንደተቻለ ተገልጿል።
በተለይ የጂግጂጋ የደምና ቲሹ ባንክ የመረጃ ስርአቱን ዲጂታላይዝ የማድረግ ስራን ዶ/ር ሊያ ታደሰ በጉኝቱ ወቅት በይፋ ያሰጀመሩ ሲሆን የምርመራ ሂደቱን በአዉቶሜሸን በመታገዝ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተመልክተዋል።