የጤና ሚኒስቴር በአዲስ መልክ ያበለፀገውን ዌብ ሳይት ይፋ አደረገ
አዲሱ ዌብ ሳይት ሁለገብና መረጃዎችን በተደራጀና ሳቢ በሆነ መንገድ ለተጠቃሚዎችና ለባለድርሻ አካላት የሚያደርስ መሆኑን የገለፁት ዌብ ሳይቱ እውን መሆኑን ያስተዋወቁት በጤና ሚኒስቴር የሚኒስትሯ ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር ዳንዔል ገብረሚካኤል ናቸው።
የቀድሞው ዌብ ሳይት መረጃ እንደልብ የማይገኝበትና ሳቢ እንዳልነበረ ቅሬታ የሚቀርብበት ነበር ያሉት ዶ/ር ዳንዔል አዲሱ ዌብ ሳይት በተገቢ መረጃዎች የተደራጀና ለአጠቃቀም ሳቢ እና ቀላል ሆኖ የቀረበ ሲሆን ማንኛውም ከሀገር ዉጪም ሆነ በሀገር ውስጥ ለሚገኙ ተገልጋዮች የኢ ላይብረሪ ፣ኦን ላይን የበጎ ፈቃድና ልገሳ አገልግሎት፣ የአስተያየት/ቅሬታ ማቅረቢያ፣ የቴሌቪዥን ቻናል፣ የዲጂታል ጤና ሲስተሞች፡ የጤና ማህበራት የጥናትና ምርምር ውጤቶችን እና ሌሎችንም ያካተተ መሆኑ ተገለጿል።
- Read more about የጤና ሚኒስቴር በአዲስ መልክ ያበለፀገውን ዌብ ሳይት ይፋ አደረገ
- Log in or register to post comments