የጤና ሚኒስቴር ለሀገር መከላከያ ሰራዊት 30 ሚሊዮን ብር እና 1.5 ሚልዮን ብር የሚገመቱ የተለያዩ የዓይነት ድጋፎችን አደረገ
በድጋፍ ርክክቡ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እንደተናገሩት አሁን ላይ አገራችን እና ህዝቦቿ ከመቼውም በተለየ ከውስጥም ከውጪም ፈተናዎች እና መሰናክሎች የገጠሟት ወቅት ላይ እንደምንገኝ ገልጸው በሁሉም መስኮች በማህበራዊ ፣ በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በውጭ ጉዳዮቻን ላይ የገጠሙን ችግሮች ለጊዜው ሊፈትኑን እና ሊከብዱን ቢችሉም እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ እነዚህ ዓይነት መሰል ውስብስብና ከባድ ችግሮች ሲገጥሙን ይህ የመጀመርያችን አይደለም፤ ቀደም ሲል ከውስጥም ከውጭም ችግሮች የገጠሙን ወቅት በነበረን አገራዊና ህዝባዊ ፍቅር፣ በነበረን መደማመጥና መግባባት፣ ሚሊዮኖች እንደ አንድ ሆነን፣ አንዱ እንደሚሊዮን ሆኖ ችግሮቹን እና ፈተናዎችን ተሻግረን ዛሬ ላይ መድረሳችን በቂ ማሳያ ነው ሲሉ የአንድነት ጥንካሬያችንን አስታውሰዋል::