ትኩረት የሚሹ የሀሩራማ በሽታዎችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ በመቀናጀት መስራት ይገባል
በሲዳማ ክልል አስተናጋጅነት በሀገራችን ለሶስተኛ ጊዜ እየተዘከረ ባለው የአለም ትኩረት የሚሹ የሀሩራማ በሽታዎች ቀንን አስመልክቶ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ባስተላለፉት መልእክት እንደ ዝሆኔ/ፖዶኮኒዮሲስ፣ ሊንፋቲክ ፊላሪያሲስ፣ ሀይድሮ ሲል፣ ሌሽሚያሲስ የመሳሰሉ የቆላማ እና ሀሩራማ በሽታዎች ለረጅም ዘመን ትኩረት ሳያገኙ በመቆየታቸው ዜጎችን ለተለያዩ አካላዊ፣ ስነ-ልቦናዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶች እየዳረጉ መሆናቸውን ተናግረው ይህንን ለመቀየር ጥራት ያለው የጤና አገልግሎትን በሁሉም ስፍራ ማዳረስ ረገድ ሁሉም በጤና ዘርፍ እየሰሩ ያሉ አካላት ተገቢ ትኩረት እንዲሰጡ፣ እንዲሁም በጋራ በመቀናጀት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።