የኢትዬጵያ ሕብረተሠብ ጤና ኢንስቲትዩት ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት 5 ሚሊዮን ብር እና ከ200 ሺ ብር በላይ የሚገመት አልባሳት ድጋፍ ተደረገ
በርክክቡ ወቅት የጤና ሚኒስቴር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ባስተላለፉት መልእክት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለሀገር ህልውና እና እያደረገ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ይህን ታሳቢ በማድረግ ያደረገውን ድጋፍ አመስግነዋል። ይህም ድጋፍ 5 ሚሊዬን ብር እና ከ200 ሺ በላይ የሚገመቱ አንሶላዎች፣ ቢጃማና ነጠላ ጫማዎች መሆኑንም ገልፀዋል።
የመከላከያ ሠራዊት ምንስትር ዴኤታ ወ/ሮ ማርታ ሊዊጂ በበኩላቸው የጤናው ዘርፍ በዚህ ፈታኝ ወቅት ለሀገር እያደረገ ያለው አበርክቶ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው አሁንም በገንዘብና በዓይነት በኢትዬጵያ ሕብረተሠብ ጤና ኢንስቲትዩት የመጣው ድጋፍ ለመከላከያ ሠራዊት የሚሰጠው አገልግሎት እጅግ ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽ በመከላከያ ሰራዊት ስም አመስግነዋል።