የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የቲቢ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በጋራ ሊሰሩ ይገባል
16ኛው አመታዊ የቲቢ ምርምር ጉባኤ ላይ ከተገኙ የአጎራባች ሃገራት ተወካዮችጋር የቲቢ በሽታን መከላከልና መቆጣጠር በተመለከተ የጎንዮሽ ውይይት ተካሂዷል።
አጎራባች ሀገራት በሚዋሰኑባቸው አከባቢዎች ተመሳሳይ ማህበረሰብ የሚገኝባቸው በመሆናቸው እና በተለይም አርብቶ አደር በሚበዛባቸው የምስራቅ አፍሪካ አጎራባች አከባቢዎች የቲቢ በሽታ ህክምናን ለመስጠትም ሆነ ክትትል ለማድረግ አዳጋች በመሆኑ ሃገራቱ በጋራ መስራታቸው ጠቀሜታው የጎላ ይሆናል።
በአጎራባች አከባቢዎች ያለው ነባራዊ ሁኔታን የሚያመለክት በቂ መረጃ አለመኖር እና የግብአት ውስንነት ማነቆ መሆኑን ተወካዮች አውስተው የምርምር ተግባራትን በስፋት መስራት፣ ትብብርን ማጠናከርና ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ ከፍተኛ ሃላፊዎችን ማስገንዘብና የሚድያና ተግባቦት ፕላትፎርም ተፈጥሮ በትኩረት በጋራ መስራት አስፈላጊ እንደሆነ ጠቁመዋል።
- Read more about የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የቲቢ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በጋራ ሊሰሩ ይገባል
- Log in or register to post comments