በኢትዮጵያና በአጎራባች ሀገራት የጤና ስርዓትን ለማጠናከር የሚያግዙ ስምምነቶችና እርዳታዎች ተደረጉ፡፡
የሀገራችን የጤና ስርዓትን በማጠናከር የሀገር ውስጥና ድንበር ተሻጋሪ የጤና በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የበለጠ ተግቶ መስራት እንዲቻል በዛሬው እለት በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በአውሮፓ ህብረት ድጋፍና በምስራቅ አፍሪካ በየነ-መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ)እንዲሁም በዩኖፕስ አስተባባሪነት የኢትዮጵያንና የአጎራባች ሀገራት የጤና ስርዓትና የኮቪድ-19 ምላሽን ለመደገፍ ለኢትዮጵያ የጤና ሚኒስቴር በተደረገው ልዩ ልዩ የጤና አምቡላንሶችና ቁሳቁሶች ርክክብ እና የመግባቢያ ሠነድ ፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ የጤና ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ እንደገለጹት የተሻለ ጤናን መኖር የሚቻለው የተሻለ የጤና ሥርዓት ሲገነባ እንደሆነ በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡