ዲጂታላይዝድ የታካሚዎች የጤና መረጃ አያያዝ መተግበሪያ ‹‹ዌልነስ ፓስ›› የሙከራ ትግበራ ስምምነት ተፈረመ
የጤና ሚኒስቴር መተግበሪያውን ወደ ስራ ለማስገባት ከማስተር ካርድ፣ ከጋቪ እና ከጄ ኤስ አይ ጋር ዛሬ ስምምነት ተፈራርሟል።
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ በሁለተኛው የጤናው ዘርፍ እቅድ ውስጥ በመረጃ ላይ የተመሰረተ የውሳኔ አሰጣጥ ስርዓት ለማጠናከር ጥራት ያለው መረጃ ማሰባሰብ፣ መተንተን እና መጠቀም ቁልፍ ተግባራት አድርጎ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸው በዚሁ ወቅት ዲጅታል መተግበሪያው በሙከራ ደረጃ መጀመሩ በጤናው ዘርፍ ያለውን የመረጃ ስርዓት ለማዘመን እንደሚረዳ ገልፀዋል።
የታካሚዎችን የጤና መረጃ ስርዓት ፍሰትን ለማቀላጠፍ ማስተር ካርድ ‹‹ዌልነስ ፓስ›› የተባለው የዲጅታል መላ የሙከራ ትግበራውም በተመረጡ የጤና ተቋማት በ15 ወራት ውስጥ ለአንድ ሚሊዮን ተገልጋዮች ለማዳረስ የታለመ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡