የኮሪያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) ለጤና ሚኒስቴር የእናቶችና ጨቅላ ህጻናት ጤናን ለማሻሻል የሚረዳ የህክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ::
የኮሪያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) ለጤና ሚኒስቴር 31,076,584 ብር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ,በቤንሻንጉል ጉሙዝ እና አፋር ክልሎች የእናቶችና የጨቅላ ህጻናት ጤናን ለማሻሻል በዩኒሴፍ አመቻችነት የኮሪያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) ባደረገው የገንዘብ ድጋፍ የህክምና መሳሪያዎች እና ለትራንስፖረት አገልግሎት የሚውሉ ሞተር ሳይክሎችን ለጤና ሚኒስትር አስረክቧል፡፡