በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ስራ ተጀመረ
የጤና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር ዛሬ በልደታ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 5 የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስጀምረዋል።
መርኃ ግብሩ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አየለ ተሾመ እና የተጠሪ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ተገኝተዋል።
ጤና ሚኒስቴርና ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን በዘንድሮው መርሐግብር 12 አቅመ ደካሞችን በአዲስ አበባ እና 5 ቤቶችን በክልሎች የሚገነቡ ሲሆን ይህም የእርስ በእርስ የመደጋገፍ ባህልን የሚያዳብርና ለመጪው ትውልድም መልካም እሴትን የሚያሸጋግር ታላቅ በጎ ስራ ነው ብለዋል ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፡፡
- Read more about በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ስራ ተጀመረ
- Log in or register to post comments