የእናት ጡት ወተት የህይወት ምግብ!
“ምቹ ሁኔታ ለሚያጠቡ እናቶች፤ እናስተምር፤ እንደግፍ!!” በሚል መሪ ቃል የዘንድሮው የጡት ማጥባት ሣምንት በዓለም ለሰላሳኛ በሀገራችን ደግሞ ለአስራ አራተኛ ጊዜ እየተከበረ ነው፡፡
የሥርዓተ ምግብ ችግሮች በዓለም ላይ በየዓመቱ ወደ አምስት ሚሊዮን ሕፃናት ህመምና ሞት ምክንያት ነው ያሉት የጤና ሚኒስቴር የእናቶች ህፃናት እና የስርዓት ምግብ ዳይሬክተር ዶ/ር መሰረት ዘላለም ከፅንስ ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት ዕድሜ ባለው ጊዜ ማስተካከል ካልተቻለ መቀንጨር እና ሌሎች የምግብ አለመመጣጠን ችግሮች ሊከሰት እና በቀጣዩ የእድሜ ክልል ከትውልድ ወደ ትውልድ ሊተላለፍ የሚችል አመጋገብ ችግር ይሆናል ብለዋል።
- Read more about የእናት ጡት ወተት የህይወት ምግብ!
- Log in or register to post comments