የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር የ2015 እቅድ ማስተዋወቂያ እና የምክክር መድረክ ተካሄደ
የዘንድሮው አመታዊ አገራዊ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር እቅድ የክልል እና ከተማ መስተዳድር ጤና ቢሮዎችን እና ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር ጽህፈት ቤቶችን ሴክተር መስሪያ ቤቶችን እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር የተዘጋጀ ሲሆን፤ የ2014 በጀት አመት አፈጻጸምን በመገምገም 2015 በጀት አመት እቅድ ዝግጅት የጋራ ለማድረግና ቀጣይ እርምጃዎችን ለማፋጠን ይረዳ ዘንድ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ መሆኑን በጤና ሚኒስቴር የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ህይወት ሰለሞን ገልጸዋል፡፡
በተለያዩ አካላት ሲመራ የነበረው የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር ስራ አዲስ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በአንድ እንዲመራ መደረጉ መልካም ነው ያሉት ዳይሬክተሯ፤ በአለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጠውን አቅጣጫ በማሳካት የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭትን በ2030 ለማስቆም መስራት ይገባል ብለዋል፡፡