የሕግ አገልግሎት ሥራ አስፈፃሚ

  1. ስለ ሥራ አስፈፃሚው መግለጫ:-

ሚኒስቴር መ/ቤታችን የፌደራል መንግስት አስፈፃሚ አካላትን ስልጣን እና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀጽ 16(16) መሠረት የተቋቋመ ተቋም ነው፡፡

ሚኒስቴር መ/ቤቱ በዚህ አንቀጽ መሠረት እነደ አንድ የፌደራሉ መንግስት አስፈፃሚ አካል ከተቋቋመ በኋላ የተቋሙ ስልጣን እና ተግባር ደግሞ በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 35 መሠረት እንዲወሰን ሆኗል፡፡ በዚህም መሠረት ሚኒስቴር መ/ቤቱ የመከላከል፤የማከም እና መልሶ የማቋቋም መንገዶችን በመጠቀም የዜጎችን ጤና የመጠበቅ ሥራ ላይ ስልጣን እና ተግባር እንዲኖረው ተደርጓል፡፡

እነዚህን ስልጣን እና ተግባራት በአግባቡ እና በውጤታማነት ለመወጣት ይችል ዘንድ ሚኒስቴር መ/ቤቱ በተለያዩ የስራ ክፍሎች የተዋቀረ እና የተደራጀ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ከእነዚህ የሥራ ክፍሎች መካከል ደግሞ የሕግ አገልግሎት ሥራ አስፈፃሚ አንዱ እና ዋነኛው ነው፡፡

የሕግ አገልግሎት ሥራ አስፈፃሚ ከሚያከናውናቸው ዋና ዋና ተግባራት መካከል ተቋሙን በፍ/ቤት መወከል፤የሕግ ሠነዶችን ማርቀቅ፤ በውሎች እና ሌሎች የሕግ ጉዳዮች ላይ የሕግ ምክርና አስተያየቶችን መስጠት፤ እንዲሁም ለሕግ የበላይነት መስራት የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

በዚሁ መሠረት የሕግ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚው በማናቸውም ተቋሙ በሕግ የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር ለመወጣት በሚያደርጋቸው ጥረቶች ላይ አስፈላጊውን ሙያዊ ድጋፍና እና እገዛ ማድረግ ዋና ሥራው ነው፡፡

  1. ዋና ዓላማ:-

ሚኒስቴር መ/ቤቱ በሕግ የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር በአግባቡ ለመወጣት በሚያደርገው ጥረት ተቋሙን በዘመነ እና ከፍተኛ ጥራ ባለው የሕግ አገልግሎት መደገፍ ነው፡፡

  1. የሥራ አስፈፃሚው ዋና ዋና ተግባርና ኋላፊነቶች:-

                   4.1. የሕግ ሠነዶችን ማርቀቅ (አዋጆችን, ደንቦችን, መመሪያዎችን, ውሎችን, ወዘተ.)፤

                  4.2. የሕግ ምክርና አስተያየት መስጠት፤

                  4.3. ተቋሙን በፍ/ቤቶች ወክሎ በመገኘት የፍርድ ቤት ክርክሮች ላይ ክትትል ማድረግ፤

                  4.4. በሕግ ጉዳዮች ላይ ስልጠናዎችን እና የሕግ ግንዛቤ ፈጠራ ስራዎችን መስራት፤